የኛ አጎራባች የሆኑት የአበባ እርሻ ድርጅቶች ኤኪው ሮዝስ፣ ብራም ሮዝስ፣ ሀርበርግ ሮዝስ እና ዝዋይ ሮዝስ የተለያዩ አዳዲስ የሕክምና መርጃ መሣሪያዎች በርዳታ ለሼር ሆስፒታል በቅርቡ በስጦታ ተሰጥተዋል። በዚህም መሠረት የሆስፒታላችን ሠራተኞች የልብ መመርመሪያ መሣሪያ (ኢሲጂ)፣ ሦስት የታካሚ ሰውነት መቆጣጠሪያ መሣሪያዎች፣ እና የማዋለጃ አልጋ በእጃቸው ለማስገባት ችለዋል። ለሰጡን ድጋፍና በተለይም የድንገተኛ ሕሙማን ክፍላችንን ለማጠናከር ላበረከቱት አስተዋፅኦ እነዚህን ኩባንያዎች በዚህ አጋጣሚ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ልናቀርብላቸዉ እንወዳለን።
ዝዋይ ውስጥ በሚገኙት 5 የአበባ እርሻዎች ዉስጥ የሚሠሩ በቁጥር 20000 የሚጠጉ ሠራተኞች ነጻ ሕክምና በሼር ሆስፒታል በኩል ያገኛሉ ፡፡ እንዲሁም በየዓመቱ ቁጥራቸው ከ 100.000 የሚልቅ ፣ ከሠራተኞች፣ ከተማሪዎችና ከአካባቢው ማኅበረሰብ የተውጣጡ ታካሚዎች በሆስፒታሉ ውስጥ የሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ።