ዘላቂነት

ሰው ሠራሽ ረግረጎች

ዝግ የውሃ ሲስተምና ለማጥለልና ማጣራት የተገነቡ ሰው ሠራሽ ረግረጎች

ሼር ኢትዮጵያ ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል በልዩ ሁኔታ ውሃን አጥልሎ መልሶ ለመጠቀም የተዘጋጀ ልዩ ዝግ የውሃ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ የሉፕ ሲስተም ይጠቀማል። ሰው ሠራሽ ረግረግ ተብለው የሚጠሩት ዲዛይን የተደረጉት ኔዘርላንድ በሚገኘው የዋገኒንገን ዩኒቨርሲቲና የምርምር ማዕከል ውስጥ ነው። እነዚህ ሰው ሠራሽ ረግረጎች ሁሉንም ቆሻሻ ውሃ ያጣራሉ። ከማጣራት በኋላ ውሃው የፅጌረዳ አበባ ተክሎችን በመስኖ ለማልማት መልሶ ጥቅም ላይ ይውላል።

በመጀመሪያ ሁሉንም ቆሻሻ ውሃ፣ ፍሳሽ ውሃ፣ ከርጭት መሥመሮች የሚቀር ውሃ፣ የባልዲ ውሃ፣ ከቱቦዎች የሚገኝ፣ የሽንት ቤት ውሃ፣ ወዘተ እንሰበስባለን። ሸምበቆ መሰል ተክሎችን የሚይዙ ካርቦን ላይ የተመሠረቱ የማጣሪያ መደቦች በግሪን ሀውሶች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ። ሸምበቆ የተፈጥሮ ማጣሪያ ነው። የእነዚህ ተክሎች ሥሮች ውሃውን ያጣራሉ። በተፋሰሶች ውስጥ የሚጨመረው ዓሣ ጤናማና የተነቃቃ መሆን የውሃውን ንጹሕነት ያረጋግጣል። ከዚያም ውሃው ወደ ቮኮም (የመስኖ ማሠራጫ ሲስተሙ) የሚፈስ ሲሆን ከዚህም የፅጌረዳ አበባ ተክሎችን በመስኖ ለማልማት መልሶ ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ ዝግ የሉፕ ሲስተም ውሃ ወደ ሐይቅ እንዳይፈስ ይከላከላል።

ከEcofyt፣ ዋገኒንገን ዩኒቨርሲቲ፣ Koppert፣ FSIና IDH ጋር በሚደረግ የጋራ ጥረት ይህን ዕውቀት በስፋት ለማቅረብ ተችሏል። ይህም በብዙ አገራት የተለያዩ ሰው ሠራሽ ረግረጎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ አስችሏል።

የሥራ አብነታዊ ጥናት

እ.ኤ.አ በ2019 ዓ.ም IDH የፀረ ተባይ ሙያተኛ ለሆኑት ለ Keith Jones (ኪዝ ጆንስ) የፕሮጀክቶች ጣልቃገብነቶችና የተዋወቁ ፈጠራዎች የቴክኒክ ባሕሪያት ላይ ትንተና እንዲያካሂዱ ተልዕኮ ሰጥቷቸው ነበር። ፕሮጀክቶቹ በሁለት ጭብጦች ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ እነዚህም፦ ፀረ ተባይ በሐይቅ ላይ የሚያደርሰውን ብክለት ለመቀነስ ሰው ሠራሽ ረግረግ መገንባትና የሴንቴቲክ ኬሚካል ፀረ ተባዮች መጠቀምን በሚተካ የተፈጥሮ መቆጣጠሪያ (ባዮ ቁጥጥር) ላይ ተመሥርተው የሚካሄዱ የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር (IPM) አሠራሮች ናቸው።

ይሄጥናት እንዳረጋገጠው ከሆነ የ IPMን ልምዶች ጋር እርስ በእርስ የሚደጋገፉ በመሆናቸው የኬሚካል ፀረ ተባዮችን መቀነስ ከፍ ወዳለ የሰው ሠራሽ ረግረጎች ውጤታማነት የሚመራ ከመሆኑም ባሻገር ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የሠራተኞችና የአካባቢ ደኅንነት ሥጋትን በእጅጉ እንደሚቀንስ ደምድሟል።

በመቀጠል፣ ተጨማሪ የጽሑፍ ምርምር የክልል የማምረት ደረጃ ሁኔታን ከሰው ሠራሽ ረግረጎችና IPM ቴክኖሎጂ ላይ የሚታየው አዳዲስ የልማት ግኝቶች ጋር የሚያያይዘው ሲሆን፣ የሰው ሠራሽ ረግረጎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያበረታታና በአሁኑ ጊዜም የሚገኝና አዳዲስ ተፈጥሮን በመጠቀም የሚደረግ የመቆጣጠሪያ አማራጭ በአካባቢው እንዲለማ ያመቻቻል።

የጠብታ መስኖ፦ ውሃ አያባክንም

የጠብታ መስኖ በሁሉም ግሪንሀውሶቻችን ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል። የጠብታ መሥመር ትናንሽ ቀዳዳዎች ያሉት የፕላስቲክ ውሃ ማጠጫ ትቦ ሆኖ በፅጌሬዳ መደቦቹ ውስጥ ይከተታል። ከዚህ የሚፈሱት ትናንሽ ጠብታዎች የፅጌሬዳ አበባ ተክሎቹን ውሃ እንዲጠጡ ይረዳሉ። ይህ እጅግ ውጤታማ የውሃ አጠቃቀም ዘዴ ሲሆን ከፉሮ መስኖ አንጻር ሲታይ ይበልጥ በተሻለ ደረጃ ብዙ ውሃ ለመቆጠብ ያስችላል። በጠብታ መስኖ በመጠቀም ‘ከያንዳንዱ ጠብታ ተጨማሪ ሰብል’ ማምረት ችለናል። በጠቅላላው በግሪን ሀውሶቻችን ውስጥ ከ4,800 ኪሎሜትሮች በላይ የጠብታ ውሃ መሥመር አለን! ከዚህ በተጨማሪም ሁሉም በቦይ ተሰብስቦ የሚጠራቀመው ውሃ ለመስኖ እርሻ ጥቅም ላይ ይውላል። በዚህ መልኩ ከሐይቅ ወይም ወንዝ የሚፈሰውን ውሃ እንቀንሰዋለን።

የሰው ሠራሽ ረግረግ 360 ዲግሪ ምስል