ሼር ኢትዮጵያ ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር በዓለም ትልቁ የፅጌሬዳ አበባ አምራች ነው

ሼር ኢትዮጵያ ፅጌሬዳ አበባ አምራች ነው። በሦስቱ እርሻዎቻችን ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 12,500 ገደማ የሆኑ ሠራተኞቻችን ያመረቷቸውን አበባዎች ከሰበሰቡ በኋላ ደረጃ ሰጥተው ለገበያ ያቀርባሉ። በየቀኑ ከ2.5 እስከ 4 ሚሊዮን የሚደርስ የፅጌሬዳ አበባ ወደ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ከተጓጓዘ በኋላ ወደ የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ይሠራጫል። በዚህም ምክንያት በዓለም ደረጃ ትልቁ የፅጌሬዳ አበባ አምራችና ለአውሮፓ ደግሞ ዋንኛው የሮዝ አበባ አቅራቢ ለመሆን ችለናል።

በዋንኛነት መታየት ያለበት ጉዳይ

ሼር ኢትዮጵያ በሚሠራው ሥራ ከካርቦን ልቀት ነጻ የሆነ ድርጅት ነው!

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከካርቦን ልቀት ነጻ የመሆን መርህ ከሼር ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዓላማዎች መካከል አንዱ ሆኗል። እንደ ኩባንያ፣ ከካርቦን ነጻ የመሆን ደረጃ ዕውቅናን ስለተጎናጸፍን በሥራችን በእጅጉ እንኮራለን። ይህም ማለት ለገበያ የምናቀርባቸው ፅጌሬዳ አበባዎችና የሽያጭ ክንውኖቻችን ከማናቸውም ካርቦን ልቀት ነጻ የሆኑ ናቸው ማለት ነው።

ስለ ከካርቦን ልቀት ነጻ መሆን ምንነት ተጨማሪ ያንብቡ
ዘላቂነት

የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር

ፅጌሬዳ በምናመርትበት ጊዜ የአበባ በሽታና ተባይ አይቀሬ የሆነ ችግር ነው። ይሁን እንጂ፣ እነዚህ በሽታዎችና ተባዮችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል ያንኑ ያክል በቂ ዕውቀት አለን። ሼር ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋዊና ከኬሚካል የፀዱ ተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይጠቀማል።

ተጨማሪ ያንብቡ
ከተመድ (UN) የዘላቂ የልማት ግቦች አንጻር ያበረከትናቸውን አስተዋፅኦዎች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ይፈልጋሉ?

የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) “ለሁላችንም የተሻለና የበለጠ ዘላቂነት ያላትን ዓለም ለመፍጠር እንድንችል እንደ መነሻ ሐሳብ ሆኖ እንዲያገለግል” የተዘጋጀ በሥሩም እርስ በርሳቸው ተያያዥነት ያላቸው 17 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ መሆን ያለባቸውን ግቦች የያዘ ነው። ከሼር ኢትዮጵያ አንጻር ሲታይ ከእነዚህ ግቦች መካከል በ15ቱ ላይ የማይናቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገናል።

የኛን አስተዋፅኦዎች ይመልከቱ
ቪዲዮ