ዘላቂነት

ማዳበሪያ ማዘጋጀት

የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለዝውውር አስተዋጽኦ ያደርጋል

በሼር ኢትዮጵያ ከደረጃ ምደባ፣ የሰብል ማረም፣ መከርከምና ነቅሎ መጣል የሚወጣውን ቆሻሻ/ተረፈ ምርት ወደ የተፈጥሮ ፣ዳበሪያነት እንቀይራለን። የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት የተፈጥሮ ኦርጋኒክ ነገሮችን ለአካባቢ ጠቃሚ ወደሆኑ መጠቀሚያዎች/ትግበራዎች የመቀየር ሂደት ነው። ሂደቱ ኦርጋኒክየሆኑ ነገሮችን ወደ ትናንሽ ንጥረ ነገሮች ለመሰባበር እንደ ባክቴሪያ፣ አክቲኖሚስና ፈንገስ የመሳሰሉ ጥቃቅን ተህዋሲያንን ይጠቀማል።

በተፈጥሮ አካባቢዎች ውስጥ ከተክሎች ላይ የሚረግፉ ቅጠሎችና ቅርንጫፎች የተክሎች ሥሮችን የሚከላከልና ለተፈጥሮ እጅግ ዋነኞቹ መልሶ ተጠቃሚዎች ማለትም ትሎች፣ ነፍሳቶችና በዓይን ሊታዩ የማይችሉ ጥቃቅን ተህዋሲያን መኖሪያነት የሚያገለግል የበለጸገ፣ እርጥብ ብስባሽ ይሠራሉ። የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት ደረቅ ቆሻሻን ለጠቃሚ አገልግሎት የማከምና በሽታ አስተላላፊ ተህዋሲያንን፣ በሽታዎችንና አላስፈላጊ አረምን የማስወገድ አዋጭ አሠራር ነው። የአየር ሁኔታውን፣ እርጥበትንና ንጥረ ነገሮችን በአግባቡ በመቆጣጠር የማዳበሪያ ዝግጅት ሂደቱ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ኦርጋኒክ ቁሶች በንጽጽር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ፍግነት እንዲቀየሩ ያደርጋል። በእኛ ሁኔታ ይህ ከስድስት እስከ ስምንት ሳምንታት የሚወስድ ሥራ ነው።

ጠቀሜታዎች

በተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅቱ ወቅት ጥቃቅን ተህዋሲያኑ ኦርጋኒክ የሆነውን ነገር ለመመገብ ኦክስጂን ይመገባሉ። ሙሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ከፍተኛ መጠን ያለው ሙቀት የሚፈጥር ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ካርቦን ዳይኦክሳይድና ውሃ በትነት ወደ አየር ይቀላቀላሉ። በትነት የሚወጣው ካርቦን ዳይኦክሳይድና ውሃ የኦርጋኒክ ነገሮቹን የመጀመሪያ ክብደት ግማሽ ያክሉን የሚደርስ በመሆኑ ወደ ማዳበሪያነት መቀየሩ ወደ ብስባሽነት የሚቀየሩትን ግብአቶች ይዘትና ክብደት ይቀንሰዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት ጠቀሜታዎች የሚከተሉት ናቸው፦

  • የአፈሩን መዋቅርና ለምነት ያሻሽላል፣
  • ቀስ በቀስ የተክል ንጥረ ነገሮችን ይለቃል፣
  • የተክሉን ሥሮች ጠንካራ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
  • ጥሩ የአልሚ ነገሮች ምንጭ ነው፣
  • ለአካባቢ ተስማሚ ነው።

ሁሉም የተፈጥሮ ማዳበሪያ የፅጌረዳ አበባዎቹን ለመመገብ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ይህም ከአበባ ተከላ በፊት ይጨመራል።