ስለ እኛ ማንነት

ኩባንያችንና የሚገኝባቸው ቦታዎች

overview river in ziway

ሼር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ

ሼር ኢትዮጵያ የፅጌረዳ አበባ አምራች ነው። የፅጌረዳ አበባዎቹ ከብረት መዋቅርና የፕላስቲክ ሽፋን በተሠሩ ግሪንሀውሶች ውስጥ ይበቅላሉ። ወደ 12,500 የሚጠጉ ሠራተኞች በሦስት እርሻዎች የፅጌረዳ አበባዎችን ይተክላሉ፣ ይሰበስባሉ፣ ደረጃ ይመድባሉ እንዲሁም ያሽጋሉ። በየዕለቱ ከ2.5 እስከ 4 ሚሊዮን የፅጌረዳ አበባዎች ተቀነባብረው/ተዘጋጅተው አዲስ አበባ ወደ የሚገኘው አየር መንገድ የሚጓጓዙ ሲሆን ከዚህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፓ ውስጥ ወደሚገኙ ተጨማሪ መዳረሻዎች ይላካሉ። ይህም የዓለማችን ትልቁ የፅጌረዳ አበባ አብቃይና የአውሮፓ ትልቁ የፅጌረዳ አበባዎች አቅራቢ ያደርገናል።

ኢትዮጵያ የፅጌረዳ አበባዎችን ለማብቀል እጅግ በጣም ምቹ ሁኔታዎች አሏት፤ ለአብነትም፦ ለም አፈር፣ ተስማሚ የአየር ንብረት፣ በቂ የዝናብ ውሃና ተስማሚ ከፍታ አላት። የአትክልት/ አበባ ዘርፉ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በጣም ወሳኝ ነው። ለዚህ ደግሞ ሼር ኢትዮጵያ ዋነኛው ተዋናይ ሲሆን ወደ 4% የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል።

አንዳንዳንድ ትኩረት የሚስቡ ዝርዝሮች፦