ማኅበራዊ ኃላፊነት

ሠራተኞች

ሼር ኢትዮጵያ ለሠራተኞቹ ከፍተኛ ምሥጋናውን ያቀርባል። የዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) ያወጣው ደምብ ላይ የተመሠረተውን The Ethical Trading Initiative Base Code (ሥነ ምግባርን የጠበቀ ንግድ ኢኒሺየቲቭ መነሻ ደንብ)ን ተግባራዊ አድርገናል። ሁሉም የሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሞችን ያገኛሉ።

ሁሉም ሠራተኞቻችን ቋሚ የቅጥር ውል ይሰጣቸዋል። ለሼር ኢትዮጵያ መሥራት ማለት ፍትሐዊ ደመወዝ ከነ ማካካሻዎች፣ ጡረታና ነጻ የሕክምና እንክብካቤ የመሳሰሉ ሳቢ የክፍያና ጥቅማ ጥቅም ጥቅሎች ማግኘት ማለት ነው።

ሠራተኞቻችን በነጻነት የሥራ ማኅበር መቀላቀል ይችላሉ። Collective Bargaining Agreement (CBA) (የኅብረት ድርድር ስምምነት) ያለን ከመሆኑም በተጨማሪ የሠራተኞቻችን ልጆች በ የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት በነጻ ትምህርታቸውን መከታተል ይችላሉ (ትምህርት ቤት መግቢያ ዕድሜ 4 ዓመት ነው)።

ለሁሉም አዲስ ሠራተኞች በቅጥራቸው የመጀመሪያ ቀን ገለጻና የጤናና ደኅንነት ሥልጠና ይሰጣቸዋል። ለሠራተኞች እንደየሥራ መደቦቻቸው ተገቢ የግል መከላከያ መሣሪያዎች (PPE) ይሰጣቸዋል።
ሠራተኞች በሼር ኢትዮጵያ ክበብ በሚቀርበው የመዝናኛ አገልግሎትና በአግባቡ በተሟላው የሼር ኢትዮጵያ ስታዲየም በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መዝናናት ይችላሉ።

ሠራተኞቻችን የተለያዩ ኮሚቴዎችን ሊቀላቀሉ ይችላሉ፦

  • የሠራተኞች ማኅበር (የሼር ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግ.ማ መሠረታዊ የሠራተኞች ማኅበር)
  • Fairtrade Premium Committee (የርትዓዊ ንግድ ፕሪሚየም ኮሚቴ )
  • የሥርዓተ ጾታ ኮሚቴ
  • የሥራ ላይ ደኅንነትና የጤና ኮሚቴ
  • የስፖርትና መዝናኛ ኮሚቴ
  • የፀረ ኤድስና የሥነ ተዋልዶ ጤና ኮሚቴ
  • የቅጥር ኮሚቴና የሥነ ምግባር ኮሚቴ