የሙያ ዘርፍ

አስተዳደርና ድጋፍ

የዕለት ከዕለት ሥራዎቻችን ለማከናወን የሚያስችል ውጤታማ አስተዳደርና የሥራ ድጋፍ ሰጪ መኖር ለኩባንያችን ወሳኝ ነው። አብዛኛዎቹ ሥራ አስኪያጆቻችን በአገር ውስጥ የተማሩና ሥልጠና የወሰዱ ናቸው። የሼር ኢትዮጵያ እርሻዎች በግብርና ሙያ፣ ፋይናንስ፣ የሰው ሀብት /HR/፣ አይቲ፣ ግዢ፣ ሕግና ሕግ ማስከበር፣ የሕዝብ ግንኙነት /PR/ና ግንኙነት፣ ግንባታና ፀጥታ መስኮች ለሠለጠኑ ባለሙያዎች የሥራ ቅጥር ያቀርባሉ።

ሠራተኞቻችንን ይተዋወቁ

ሰለሞን ሙሉጌታ/ የአይቲ ቴክኒሺያን (የፊትና ጣት ስካን/ማንበብ ኤክስፐርት)

በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
ለሼር ኢትዮጵያ መሥራት የጀመርኩት ከ8 ዓመታት በፊት ነበር።

እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
ከመጀመሪያ አንሥቶ የተቀጠርኩት በአይቲ ቴክኒሺያንነት ሲሆን ምንም እንኳን የአይቲ ሲስተሞች የበለጠ እየተወሳሰቡ የመጡ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ሙያ ላይ እየሠራሁ እገኛለሁ። ይህ ሥራዬን እንደወደው አድርጎኛል።

ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
ሼር ኢትዮጵያ በጣም ግዙፍና ዓለም ዓቀፍ ድርጅት በመሆኑ ከተለያዩ ሰዎችና ባላድርሻ አካላት ጋር የምገናኝባቸው/የምሠራባቸው ብዙ የተለያዩ ዕድሎች አሉኝ።

ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
ወደ ሼር ኢትዮጵያ ከተቀላቀልኩ ጀምሮ ብዙ ትምህርት አግኝቻለሁ። እዚህ እያንዳንዱ ቀን የተለየ ነው። አብዛኛውን ጊዜ አዳዲስ ፕሮጀክት ይኖሩናል። በድርጅቱ የተሰጡኝን ኃላፊነቶችና ሥራዬን በራሴ የማደራጀት ነጻነት እወዳቸዋለሁ።

Portrait - SOLOMON MULUGETA - technican
ሠራተኞቻችንን ይተዋወቁ

ብዙ ግርማ / ከፍተኛ የደረጃ ምደባ ሥራ አስኪያጅ

በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመርኩት ከ2009 (2001 ዓ.ም.) ጀምሮ ነው።

እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
ሥራዬን የጀመርኩት የብልሽት መዝጋቢ ሆኜ ነበር። ቀጥሎም በትዕዛዝ ተቆጣጣሪነት የሠራሁ ሲሆን በኋላም የአበባ ጥራት ተቆጣጣሪ ተደርግኩ። አሁን በአራት መሥመሮች (ደረጃ ምደባ ክፍሎች) የሚካሄዱ አጠቃላይ የደረጃ ምደባ ሥራዎችን እመራለሁ።

ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
የተማርኩት ትምህርትና ዝንባሌዬ ግብርና እንደመሆኑ ለሼር ኢትዮጵያ ለመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ።

ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
ከራሴ ተሞክሮ በመነሣት ማንኛውም ሰው ጠንክሮና በባለቤትነት ስሜት ለመሥራት ዝግጁ ከሆነ ኩባንያው ለራሱም ሆነ ለዚህ ሰው ጠቃሚ የሆኑ ኃላፊነቶችን ለመስጠት ፍቃደኛ እንደሆነ አውቃለሁ።