ስለ እኛ ማንነት

ክፍት የሥራ ቦታዎች

Working at Sher | Vacancies
ክፍት የሥራ ቦታዎች

ለሼር ኢትዮጵያ ቢሠሩ ምን ጥቅም ያገኛሉ?
የሼር ኢትዮጵያ ስኬታማነት በታታሪነት በሚሠሩት ሠራተኞቻችን ጥረት ላይ በእጅጉ የተመረኮዘ ነው። አስደሳችና የሥራ ፍላጎትን አነቃቂ የሥራ መደቦችን የማቅረብ ቁርጠኛ አቋም አለን። ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው የሥራ ቅጥር ሁኔታዎችን እና ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅማ ጥቅሞችን እናቀርባለን። አብዛኛዎቹ ሠራተኞቻችን የሞያ ዕድገት ጉዟቸውን የሚጀምሩት በሥራ ላይ ሆነው እየሠሩና እየተማሩ ነው፤ ሠራተኞቻችን ለሼር ኢትዮጵያ በሚሠሩበት ወቅት እራሳቸውን እንዲያሳድጉ እናበረታታቸዋለን።

ሥራ ለመቀጠር እንዴት ማመልከት ይቻላል?
በሠራተኛ ቅጥር ሂደት ወቅት ዋንኛ ትኩረታችን በአበባ እርሻዎቻችን ላይ ተቀጥረው በሚሠሩ ሙያዊ ሥልጠና የሌላቸውና በከፊል የሠለጠኑ ሠራተኞች ላይ ነው። ክኅሎት ያላቸውን ሠራተኞች ለመቅጠር በራችን ክፍት ሲሆን ለእነዚህ ሠራተኞች ቅጥር ግልጽና በእኩልነት ላይ የተመረኮዘ ዕድል እንፈጥራለን፤ እንዲሁም ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎችን በኩባንያው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና ከኩባንያው ውጭ እንለጥፋለን። ማንኛውንም መረጃ ማግኘት ከፈለጉ እባክዎ የሼር ኢትዮጵያ የሠራተኛ አስተዳደር ክፍልን በ hr@sherethiopia.com የኢሜይል መልእክት በመላክ ያነጋግሩ።