ስለ እኛ ማንነት

የሥራ ቅጥር ሁኔታዎች

Employment conditions

የሥራ ቅጥር ሁኔታዎች

ሼር ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 12,500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በተጨማሪም ሠራተኞቹ ዝዋይ ከሚገኘው የድርጅታችን የግል ሆስፒታል  የሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ። የሠራተኞቻችን ልጆች (ከክፍያ ነጻ) በሆነ መልኩ የአፀደ ሕፃናት፣ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማግኘት ዕድሉን አግኝተዋል  ። ሼር ኢትዮጵያ ለሁሉም ሠራተኞች የአሠሪና ሠራተኛ የኅብረት ስምምነት ሰነድ ያዘጋጀ ሲሆን ይኸውም ጡረታና ሥልጠናን፣ የጤናና ደኅንነት ደንቦች አከባበርን የሚያካትት ስምምነት ነው። በመጨረሻም በእርሻዎቻችን አቅራቢያ ለሚኖሩ በርካታ የማኅበረሰብ አባላት የሥራ ዕድል በመስጠታችና ገቢ እንዲያገኙ በማስቻላችን እንኮራለን። ለእኛ አካታችነት በእጅጉ ትልቅ ቦታ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ከ100 በላይ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሠራተኞቻችን በእኩል ደረጃ ይስተናገዳሉ። የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የተወሰነ ርዳታ እየተሰጣቸውና ከሥራ ቦታቸው ጋር እየተለማመዱ እንደ ማንኛውም ሌላ ሠራተኛ ጥሩ ሥራ ይሠራሉ።