ከቅርብ ዐመታት ወዲህ ከካርቦን ልቀት ነጻ መሆን ከሼር ኢትዮጵያ የአካባቢ ዓላማዎች መካከል አንዱ ነው።
በቅርቡ እንደ ኩባንያ ከካርቦን ልቀት ነጻ የመሆን ደረጃ ላይ መድረሳችንን ስንገልጽላችሁ ኩራት እየተሰማን ነው። ይህ ማለት በፅጌረዳ አበባ ማምረትና ሽያጭ ረገድ የነፍስ ወከፍ የተቋም የካርቦን ልቀት መጠናችን ከካርቦን ልቀት ነጻ ደረጃ ላይ ደርሷል። እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ የቻልነው የፅጌረዳ አበባዎችን ከማምረትና ማጓጓዝ፣ የማምረቻ እቃዎችና የግብርና ግብዓቶችን መጠቀም ጋር ተያያዥ በሆኑ ሥራዎች ላሐይ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት መጠንን በማመጣጠን ብቻም ሳይሆን መኪናዎችና የኤሌክትሪካል ጀነሬተር በመጠቀም ምክንያት የሚፈጠሩ ልቀቶችንም በማመጣጠን ነው። በዚህ ጉዟችን ላይ የካርቦት ልቀቶቻችንን በማስላትና በማረጋገጥ ረገድ በ እና ድጋፍ ይደረግልናል።
ምን ያከል የካርቦን መጠን መቀነስ እንዳለበት ለመወሰን የካርቦን ልቀቶችን መወሰን ያስፈልጋል። የአበባ ምርት ዘላቂነት ኢኒሺየቲቭ/ Floriculture Sustainability Initiative (FSI) የነፍስ ወከፍ የተቋም የካርቦን ልቀት መጠን ሙከራን የተቀላቀልንበት አንዱ ምክንያት ይሄ ነው። የሁሉንም ኢትዮጵያ ውስጥና በኔዘርላንድስ የሚካሄዱ ሥራዎቻችንን ጠቅላላ የካርቦን ልቀት መጠን ለመለካትና ለማስላት አጋራችን PRé Consultancy የPEF አሠራር ዘዴንና Horti-Footprint Category Rules (በ Wageningen University የተዘጋጀውን) ተጠቅሟል። አበባ በማብቀል፣ ደረጃ መመደብ፣ ማሸግ፣ ማጓጓዝና ማቀናበር/ማሰናዳት ምክንያት የሚፈጠሩት ሁሉም ልቀቶች በልቀት ስሌቶቻችን ውስጥ ይካተታሉ። ከዚህ በተጨማሪም እንደ ማዳበሪያዎች፣ የግሪን ሀውስ ፕላስቲክና ግንባታ የመሳሰሉት የሁሉም ግብዓቶች ልቀቶችም ይካተታሉ።
ልቀቶችን በመቀነስ ትክክለኛውን የካርቦን ክሬዲቶች መጠን ለማግኘት ማረጋገጫ የተሰጠው አካል የሆነው One Carbon World ሁሉንም የልቀት ስሌቶችና ውጤቶች አረጋግጧል። One Carbon World በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ የተደረገው የ Climate Neutral Now Initiativeዓለም አቀፍ የሪሶርስ አጋር ነው። Climate Neutral Now ዓላማውን በሁሉም ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ማኅበረሰቦችን በተመሳሳይ ዓመት በፓሪስ በጸደቀው ስምምነት መሠረት ነጻ አየር ንብረት (net zero) ያላት ዓለምን መፍጠርን ለማሳካት የሚያስችሉ የአየር ንብረት እርምጃዎችን እንዲወስዱ ማበረታታትና መደገፍን መሠረት አድርጎ እ.ኤ.አ ከ 2015 ጀምሮ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል።
በሚረጋገጡት የካርቦን ልቀት አሀዞች ላይ ተመሥርቶ የካርቦን የክሬዲት የምስክር ወረቀቶች ይሰጣሉ። በእነዚህ የተረጋገጡ የካርቦን የክሬዲት የምስክር ወረቀቶች (VERs) አማካኝነት በመላው ዓለም የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይችላል። በከፊሉ የካርቦን ክሬዲቶቻችን ለLa Pitanga / Weyerhaeuser – በዑራጋይ፣ ደቡብ ዐሜሪካ ለሚካሄድ መልሶ በደን መሸፈን ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ እናደርጋለን። ይህ ፕሮጀክት ለ100 ዓመታት የሚቀጥል ሆኖ 18,000 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን በዝናባ ደን ጥምረት/ Rainforest Alliance ተረጋግጧል። ፕሮጀክቱ በተጨማሪም በFSC (ዘላቂ የላብ ዋጋ ክፍያዎችን፣ ዘላቂ የደን አስተዳደርን፣ ወዘተ ማረጋገጥ) ማረጋገጫ ያገኘ ሲሆን በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት የሚገኙት የካርቦን ክሬዲቶች የዓለም ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ መዝገብ በሆነው በVERRA ይመዘገባሉ። ቀሪዎቹ የካርቦን ክሬዲቶች ለህንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ጥቅም ላይ ይውላሉ። እያንዳንዱ ፕሮጀክት ጥብቅ የምርመራ ሂደትን የሚያልፍ ሆኖ በተባበሩት መንግሥታት በቀጥታ ቁጥጥር ይደረግበታል። ወደፊት የአፍሪካ ወይም ኢትዮጵያ የአካባቢ የካርቦን ልቀትን የማመጣጠን ፕሮጀክቶችን የመደገፍ፣ በምንሠራበት አካባቢ ላይ ለውጥ የማምጣት ህልም አለን።
ለ2019 (2011 ዓ.ም.) ልቀቶቻችንን በማስላትና በማመጣጠን ጀምረናል። በቅርቡም የ2020 (2012 ዓ.ም.) የነፍስ ወከፍ ተቋማዊ የካርቦን ልቀት መጠን ስሌቶቻችንን አጠናቀን ተመሳሳይ የማረጋገጫ ሂደትን በማለፍ ትክክለኛውን የተረጋገጠ የካርቦን ክሬዲቶች የገንዘብ መጠን እናገኛለን። የልቀት መጠኖቻችንን መቀነስ የመጀመሪያው ደረጃ ነው። የረጅም ጊዜ ህልማችን ልቀቶቻችንን በማመጣጠን መቀጠል ብቻ ሳይሆን ልቀቶቻችንን መቀነስ ነው። የካርቦን ልቀት ስሌቶች እነዚህን ልቀቶች ከየት መቀነስ እንዳለብን በተመለከተ ጠቃሚ ሐሳቦች ይሰጠናል። ለምሳሌ፦ በአልስሚር ለምናካሂደው ሥራ አሁን ወደ 100% አረንጓዴ የኤሌክትሪካል ኃይል ተቀይረናል። በተጨማሪም የፅጌረዳ አበባዎቻችንን ለማብቀል ሌሎች ዓይነት ግብዓቶችን ስለመጠቀም እያሰብን ነው።
የOne Carbon World ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) የሆኑት አንድሪው ቦወን፦ ”የዓለማችን ትልቁ የፅጌሬዳ አበባ እርሻ/አምራች የሆነው Afriflora Sher ከካርቦን ልቀት ነጻ የመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃንና የUN Climate Neutral Now ተሳትፎን ማሳካቱን ስናረጋግጥ ኩራት እየተሰማን ነው። Afriflora አሁን ልቀቶቹን ለክቶ ለማመጣት አስተዋጽኦ ለማድረጉ የወርቅ ሜዳሊያ ደረጃ ዕውቅናን ካገኙ ጥቂት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነ ሲሆን ይህም የድርጅቱን የአየር ንብረት ለውጥን የመዋጋት ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያሳያል። እንኳን ደስ ያላችሁ!”