አብዛኛዎቹ ሠራተኞቻችን የማሳና ደረጃ መዳቢ የሥራ መደቦች ሠራተኞች ሲሆኑ እነዚህ የሥራ መደቦች ከ80 በላይ የተለያዩ ዓይነት ዝርያ ያላቸው የፅጌረዳ አበባዎች የማብቀል ሥራችን መሠረት ናቸው። የፅጌረዳ አበባዎች የሚተከሉት፣ የሚበቅሉትና የሚሰበሰቡት እነዚህ ውስጥ ነው። በየዕለቱ የመልቀም፣ የመጠቅለልና የማሸግ ሥራዎች የሚከናወኑ ሲሆን በዚህም ከ2 እስከ 4 ሚሊዮን የሚደርሱ የፅጌረዳ አበባዎች ለኤክስፖርት ይዘጋጃሉ።
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመርኩት በ2014 (2006 ዓ.ም.) ነበር።
እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
ሥራዬን የጀመርኩት በግሪንሀውስ ውስጥ እንደ ጠቅላላ ሠራተኛ ሆኜ በመሥራት ሲሆን እዚህም ሥራዬ የፅጌረዳ አበባዎችን መሰብሰብ ነበር። ከ3 ዓመታት በኋላ የደረጃ ዕድገት አግኝቼ የቤተ ሙከራ ኃላፊ ሆንኩኝ።
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የምወደው እራሴንም ሆነ ቤተሰቤን ለመደገፍ የሚያስፍለኝ ተመጣጣኝ ገቢ የሚከፈለኝ በመሆኑ ምክንያት ነው። በአካባቢው ከሚገኙ ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር ሲነጻጸር ሼር ኢትዮጵያ እንደ ትምህርት ቤትና ሆስፒታል የመሳሰሉ የጥቅማ ጥቅሞች መርሀግብሮች የሚያቀርብ ከመሆኑም በተጨማሪ በማሳ ላይ እንደ IPM ዓይነት ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም መሆኑ በድርጅቱ ውስጥ በምንሠራበት ወቅት አዲስ ዕውቀት እንድናገኝ ይረዳናል።
ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
በርግጥም ሌሎች ሰዎች ወደዚህ መጥተው እንዲሠሩ የምመክር ሲሆን ለዚህም መጥተው መሥራት የጀመሩ ብዙ ሰዎችን በምሳሌነት ማቅረብ እችላለሁ።
ዝናሽ ግራሳ/ ምርት ሰብሳቢ
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመርኩት በ2020 (2012 ዓ.ም.) ነበር።
እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
ገና ጀማሪ ሠራተኛ እንደመሆኔ እስካሁን በሥራዬ ላይ የደረጃ ዕድገት አላገኘሁም።
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
ወደዚህ እንድመጣ የጋበዘኝ ቀደም ሲል እዚህ ከሚሠሩ ጓደኞቻችን መካከል አንዱ ነበር። ኩባንያው ለሁላችንም እኩል አያያዝ ያደርግልናል። በግሪንሀውሶች ውስጥ መሥራት ምንም ጭንቀት አይፈጥርም። ኩባንያው ለሠራተኞቹ ደኅንነት ጥንቃቄ ያደርጋል፤ ለአብነት ያክል ሁላችንም የሕክምና መድን ዋስትና፣ ወዘተ እናገኛለን። ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የምመርጠው በዚህ ምክንያት ነው።
ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
በሼር ኢትዮጵያ የተሰጠኝን ዕድል እወደዋለሁ። ወደ ትውልድ ቦታዬ ተመልሼ ስሄድ ሌሎች ሥራ አጥ የሆኑ ሰዎችን ወደዚህ መጥተው ለሼር ኢትዮጵያ እንዲሠሩ እመክራቸዋለሁ። ምክንያቱም እኔ በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ያገኘኋውን ዕድሎች ሌሎች ሰዎችም እንዲያገኙ እፈልጋለሁ።