ጥምር ኃይሎች
በዓለም የጽዳት ቀን ሲከበር በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎች በአንድነት ተቀናጅተው ቆሻሻን ከአካባቢያቸው ያስወግዳሉ። በየዓመቱ በተለያዩ ጊዜዎች፣ በትምህርት ቤቶቻችን፣ በሆስፒታላችንና በአዳሚ ቱሉ፣ በቆቃና በዝዋይ በሚገኙት 3 እርሻዎቻችን ዙሪያ የሚገኙ አካባቢዎችን በማጽዳት ንቁ ተሳትፎ አድርገናል። አንዳንድ ጊዜ ከአጎራባች እርሻዎች ሠራተኞችና የከተማ ማዘጋጃ ቤት የአካባቢ ጥበቃ ጽሕፈት ቤቶች ጋ በመቀናጀት አካባቢያችንን እናጸዳለን።
በእያንዳንዱ ዓመት ብዙ ቶን ቆሻሻ ከመንገዶች፣ የወንዝ ዳርቻዎችና የዝዋይ ሐይቅ ዳርቻ ላይ በማንሳት በማዘጋጃ ቤት ተለይቶ በተዘጋጀ የቆሻሻ መጣያ ወስደን እንጥለዋለን። ቆሻሻ በዓይን ሲታይ ደስ የማይል ከመሆኑ ባሻገር የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ቀስ በቀስ አካባቢን ከመበከል አልፎ በሂደት ወደ ወንዞች፣ ሐይቆችና ውቅያኖሶች ይገባል፣ የእንስሳትን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል እንዲሁም ምድራችንንና ጤናችንን ጉዳይ ላይ ይጥላል።