Overview News

የትምህርት ዓመቱ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት

20 July 2022 Aswin Endeman
በሼር ትምህርት ቤት የመዝጊያ በዓል

በዚህ ሳምንት በኛ የሼር ትምህርት ቤቶች ውስጥ የ 2014 ዓ.ም. ትምህርት ዘመንን መዝጊያ ሥነ ሥርዓት አክብረናል። በዝዋይና በአዳሚ ቱሉ በሚገኙት ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች በሥነ ሥርዓቶቹ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል። ዝግጅቶቹ በግጥም ንባብና በባህል ትርዒቶችና ጭፈራዎች የታጀቡ ደስ በሚያሰኙ ውብ ክንውኖች የታጀቡ ነበሩ። የመዋለ ሕፃናት ተመራቂ ተማሪዎች ጥቁር ጋውናቸውንና ጥቁር ባርኔጣቸውን አድርገው ለዝግጅቱ ድምቀት ሆነዋል። የሼር ሥራ አስኪያጆችና የትምህርት ቢሮ ተወካዮች በሥነ ሥርዓቶቹ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል። የዓመቱ ምርጥ ተማሪዎችና መምህራን የምስክር ወረቀትና ሽልማቶች ተሰጥተዋቸዋል። ሁለት ስኬታማ ቀናትን በአጭሩ አሳልፈናል።

በሺሕዎች ለሚቆጠሩ ሕፃናት ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ያለ ምንም ክፍያ በመስጠት ሼር ኢትዮጵያ በርካቶችን ብሩህና የተሻለ መፃኢ ጊዜን ተስፋ እንዲያደርጉ አድርጓቸዋል። የድርጅቱን አንጋፋ መሪዎች አርአያነት በመከተል ሚስተር ጌሪት እና ሚስዝ ኔል ባርንሁርን ይህ የሕፃናቱ ተስፋ እንደለመለመ እንዲቆይ ለማድረግ ቁርጠኝነታቸው አሁንም እንደተጠበቀ ነው።

በሼር ኢትዮጵያ የትምህርት ማእከል የተሰጠ የእውቅና ሽልማት በሼር ኢትዮጵያ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት በመቀበል ላይ በሼር ኢትዮጵያ የትምህርት ዓመት መዝጊያ ላይ ተማሪዎች በድምቀት ሲያከብሩ Sher Ethiopia keessatti sirna eebbaa barattoota በሼር ትምህርት ቤት የመዝጊያ በዓል በሼር ትምህርት ቤት የመዝጊያ ስነ-ስርዓት በሼር ትምህርት ቤት የዝግጅት ፕሮግራም በሼር ትምህርት ቤት የመዝጊያ ፕሮግራም