ባለፈው አንድ አመት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ እንዲሁም የወደሙ ሰብሎች እና ለሞት የተዳረጉ እንስሳት እንዳሉ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዝዋይ እንዲሁም በአዳሜ ቱሉ ዙሪያ ከተጎዱ አካባቢዎች ዉስጥ የተወሰኑትን ለመደገፍ ያህል ሼር ኢትዮጵያ ወደ 800 ለሚጠጉ አባወራዎችን ለእያንዳንዳቸዉ 25 ኪሎ ግራም የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል። ይህንንም በሼር ኢትዮጵያ ማኔጅመንት ስም ለአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ አስተዳደር አስረክቧል። ስርጭቱም በተመሳሳይ የርክክቡ እለት መካሄዱን የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አማን ሙዳ ገልጸዋል።