በቅርቡ ለሶስተኛ ጊዜ የጌሪት ኤንድ ኔል ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለአራት 12ተኛ ክፍልን ላጠናቀቁ የሼር ትምህርት ቤት ተማሪዋች ተሰጥቷል።እንደሚታወቀው የባርንሆርን ቤተሰብ የሼር ኢትዮጵያ እና የትምህርት ቤቶቹ መስራቾች ናቸው.።በየዓመቱ 4 ተማሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በመረጡት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚማሩበት ወቅት አብዛኛውን የጥናት ወጪያቸውን እና ኑሮዋቸውን ለማገዝ ይረዳ ዘንድ በስኮላርሺፕ መልክ በየወሩ ገንዘብ በሼር ኢትዮጵያ በኩል ይላክላቸዋል። የስኮላርሺፑ ዋና አላማ የተቸገሩ ሆነዉ ነገርግን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ለመርዳት የሰበ ነው።
ስለዚህም፟ ፣ተማሪ ነኢማ አስቻሌው፣ ጀሚላ ሄዴቶ፣ መሀመድ አህመድ እና ዮርዳኖስ ሻንበል ሽልማታቸውን ከወይዘሮ ሉሊት ታዴለ እና ከ ሚስተር አስዊን ኢንዴማን አጅ ተቀብለዋል። ሼር ማኔጅመንትን በመወከልም ሚስተር አስዊን ኢንዴማን አሸናፊዎቹን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት እና የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን እና ደጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ላለፉት 16 አመታት ላደረጉት ትጋት አና ላስመዘገቡት ውጤት አመስግነዋል።
ከሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተመራቂዎች ውስጥ 8 ተማሪዎች ተመርጠው 4ቱ ለስኮላሺፕ ሲሰጣቸው ሌሎች 4 ደግሞ ላፕቶፕ ተሸልመዋል ስሥነ ሥርዓቱም የተካሄደው የተማሪ ቤተሰቦች፣ የሸር ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጆች፣ የማኅበረሰብ ሽማግሌዎች፣ የሼር ትምህርት ቤት ሠራተኞች፣ የወላጅ ኮሚቴ እና በርካታ የመንግሥት የከተማዉ አመራሮች በተገኙበት ነው።
አንደሁልጊዜው ሁሉ ጌሪት ባርንሆርን፣ ባለቤታችው ፣ ልጆቻቸው ላለፉት አመታት ለሼር ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታል ላደረጉት የማይናወጥ ድጋፍ አያመሰገንን እነዚህ ተማሪዎች ሼር ኢትዮጵያ ላስመዘገበው አወንታዊ ተፅእኖ እውነተኛ ምሳሌ በመሆናቸው እጅግ ኩራት ይሰማናል ለዝዋይ እና ለአካባቢው ማህበረሰብም ተመልሰዉ አንደሚረዱ አና አንደሚጠቅሙ አምነታችን ነው ሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተመራቂ ተማሪዎቻችን በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ ብሩህ የወደፊት ህይወት እና መልካም ጊዜ እንመኝላቸዋለን።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የሼር ትምህርት ቤቶች ከ6500 በላይ ተማሪዎችን በሶስት ቦታዎች ያስተምራሉ፣ በግምት ወደ 400 የሚጠጉ ልጆች ከ 4ዓመት እድማቸው ጀምሮ በየዓመቱ ወደ ሼር ትምህርት ቤቶች ይገባሉ. ምዝገባዉም የሚከናወነው በ 50% ከሼር ሰራተኛ ልጆች እንዲሁም 50% ደግሞ ከአካባቢው ማህበረሰብ ልጆች በሚደረግ እኩል ክፈፈል ነው።