ማክሰኞ ነሀሴ 14 ከፍተኛ የድረጅቱ ሀላፊ ሚስተር ፌርሪክ ብሩንሰማ እና የኦፕሬሽን ሀላፊ ሚስተር አስዊን ኤንደመን ፣ የህብረተሰብ ተወካይ የተከበሩ እንግዳ አባ ገዳ አብዱራማን ደቀቢ ፣ የባቱ/ዝዋይ ጤና ጣቢያ ተወካይ አቶ ፈይሳ ሌንጂሶ በተገኙበት አዲስ ብራንድ ሚኒባስ አምቡላንስ ለሼር ሆስፒታል በመሰጠቱ እኛ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል.
በተካሄደው ስነስራት አባገዳ የሆኑት አብዱራማን የምስጋና ንግግር እና አፍሪ/ሼር ለሆስፒታሉ ተጨማሪ አምቡላንስ በማበርከቱ አመስግነው አምቡላንሱ ለሆስፒታሉና ለህብረተሰቡ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል.
በአፍሪ ፍሎራ/ሼር በኩል ሚስተር አስዊን ኤንደመን ይህን አምቡላንስ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ድርሻ ያላቸውን በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምቡላንሱን ለማጓጓዝ ባደረገው አስተዋፆ አመስግነዋል በመጨረሻም የሆስፒታሉ ባለሙያዎች አስፈላጊነት ፣ በቀጣይ ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ ለሰራተኞች እና ለህብረተሰቡ በቁርጠኝነት ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን እውቅና በመሰጠት የአምቡላሱን ቀልፍ ለሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ደምስ እና ለሆስፒታል ማናጀር ኑራ ነጋዮ ተረክቦዎል፡፡
በተደረገው ስነስርዓት አምቡላንሱ ለስራተኛ እና ህብረተሰቡ ለሪፈራልና ድንገተኛ ጥሪ እንደተጨማሪ አቅም እና ለህክማና ቡድንለመደበኛ ስራቸው ድጋፍ እንዲሆነ በመግለፅ አምቡላንሱ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡