ሼር ኢትዮጵያ ፅጌሬዳ አበባ አምራች ነው። በሦስቱ እርሻዎቻችን ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 12,500 ገደማ የሆኑ ሠራተኞቻችን ያመረቷቸውን አበባዎች ከሰበሰቡ በኋላ ደረጃ ሰጥተው ለገበያ ያቀርባሉ። በየቀኑ ከ2.5 እስከ 4 ሚሊዮን የሚደርስ የፅጌሬዳ አበባ ወደ ቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ከተጓጓዘ በኋላ ወደ የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ይሠራጫል። በዚህም ምክንያት በዓለም ደረጃ ትልቁ የፅጌሬዳ አበባ አምራችና ለአውሮፓ ደግሞ ዋንኛው የሮዝ አበባ አቅራቢ ለመሆን ችለናል።
ዘላቂነት
ተጨማሪ ያንብቡ
የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር
ፅጌሬዳ በምናመርትበት ጊዜ የአበባ በሽታና ተባይ አይቀሬ የሆነ ችግር ነው። ይሁን እንጂ፣ እነዚህ በሽታዎችና ተባዮችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል ያንኑ ያክል በቂ ዕውቀት አለን። ሼር ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋዊና ከኬሚካል የፀዱ ተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይጠቀማል።
ከተመድ (UN) የዘላቂ የልማት ግቦች አንጻር ያበረከትናቸውን አስተዋፅኦዎች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ይፈልጋሉ?
ቪዲዮ