ማኅበራዊ ኃላፊነት

social responsibility arena
ሠራተኞች

ሼር ኢትዮጵያ ለሠራተኞቹ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል። ሥነ ምግባርን የጠበቀ ንግድ ኢኒሺየቲቭ መነሻ ደንብ ተግባራዊ ያደረግን ሲሆን ደንቡ በዓለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) ደረጃዎች ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀ ነው። ሁሉም የሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞች ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሞችን ያገኛሉ።

ለሁሉም ሠራተኞች ቋሚ የቅጥር ውል የሚሰጣቸው በመሆኑ የቀን ሠራተኛ ወይም የወቅት የጉልበት ሠራተኞች የሉንም። ለሼር ኢትዮጵያ መሥራት ማለት ፍትሐዊ ደመወዝ ከተገቢ አበሎች፣ ጡረታና ነጻ የሕክምና እንክብካቤ ጋር ማግኘት ነው። ሠራተኞቻችን የሠራተኛ ማኅበር ለመቀላቀል ነጻነት አላቸው። በተጨማሪም የኅብረት ድርድር ስምምነት (CBA) አለን። የሠራተኞች ልጆች በበሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ያለ ክፍያ ትምህርታቸውን መከታተል ይችላሉ (ትምህርት ቤት የመግቢያ ዕድሜ 4 ዓመት ነው)። ለሁሉም አዲስ ሠራተኞች በቅጥራቸው የመጀመሪያ ቀን የጤናና ደኅንነት ሥልጠና ይሰጣቸዋል። ከሥራ ጋር ተያያዥ እንቅስቃሴዎች በሚደረጉበት ወቅት ሊያጋጥም የሚችል ሥጋትን ለመቀነስ አስፈላጊ የግል የደኅንነት መጠበቂያ አልባሳትን (PPE) እናቀርባለን።

በዝዋይ ማሳ የሚገኘው ክለባችን ሠራተኞች ምሳና እራታቸውን እንዲመገቡበት እንዲሁም የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማስተናገድ ጥቅም ላይ ይውላል።

ኮሚቴዎች

ሠራተኞቻችን የተለያዩ ኮሚቴዎችን መቀላቀል ይችላሉ፦

ለገጠራማ አካባቢዎች ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ እጥረት አለ። ይህም ሆኖ በአብዛኛዎቹ የውሃ ጉድጓዶች ውስጥ የሚጠራቀመው ውሃ ከመጠን በላይ የፍሎራይድ ይዘት ያለው ነው። እንደ ቦቼሳና ዎርጃ ዋሽጉላ ለመሳሰሉ ለአንዳንድ አጎራባች የመኖሪያ መንደሮች የውሃ መሥመሮቻቸውን እንዲያራዝሙና የውሃ ቧንቧዎችን እንዲዘረጉ የምንረዳው ለዚህ ነው። አሉቶ ጉልባ አዲስ ፕሮጀክት ነው።

ስፖርቶች

ሼር ኢትዮጵያ የራሱ የእግር ኳስ ሜዳ አለው። ስታዲሙ በሠራተኞች መካከል የሚካሄዱ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ከማስተናገድ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕሪሚየር ሊግ ቡድን የሆነውን የቡና ቡድንን ተቀብሎ በማስተናገዱ ኩራት ይሰማዋል።

ቤተ ክርስትያን

ባለፉት ጊዜያት ውስጥ ሼር ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ግንባታ ላይ የበኩሉን ልገሣ ሰጥቷል…

IDH

ከውጤታማ የቆሻሻ አወጋገድ፣ የደን ልማት፣ የተራቆቱ መሬቶችን ማሻሻል፣ አነስተኛ ይዞታ ላላቸው አርሷአደሮች ከሚሰጥ የጥሩ የግብርና አሠራሮች ሥልጠናና የባሕር አረም ቁጥጥር ጋር በተያያዙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ከIDH ጋር በትብብር እየሠራን ነው።

Sustainable Trade Initiative (የዘላቂ ንግድ ኢኒሺየቲቭ) የሆነው IDH በዓለም አቀፍ የዕሴት ሰንሰለቶች ላይ ዘላቂ ንግድን እውን ለማድረግ ከንግድ ድርጅቶች፣ ስፖንሰሮች፣ መንግሥታትና የሲቪል ማኅበረሰብ ጋር በጋራ የሚሠራ ማኅበራዊ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ዘላቂ ምርትና ንግድን ለማሳካት በአፍሪካ፣ እሲያና ላቲን አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎችና ቦታዎች ከ600 በላይ ከሆኑ ኩባንያዎች፣ CSOs፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ አምራች ድርጅቶችና መንግሥታት ጋር በጋራ ይሠራል። ድርጅቱ ለአዲስ ሥራዎች ፈጠራ፣ ለዘላቂ ኢንዱስትሪዎችና አዲስ ዘላቂ ገበያዎች የፈጠራ፣ በንግድ ሥራ የሚመሩ አቀራረቦችን አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደርጋል። እነዚህ ሁሉም የሚደረጉት እ.ኤ.አ በ2030 ዓ.ም. የዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት ይቻል ዘንድ በአየር ንብረት ለውጥ፣ የደን ጭፍጨፋ፣ የጾታ እኩልነት፣ የመኖሪያ የላብ ዋጋ ክፍያዎችና የመኖሪያ ገቢዎች ላይ ጉልህ ለውጥ ለማምጣት ነው።

FSI

FSI (የአበባ ልማት ዘላቂነት ኢኒሺየቲቭ) ቢያንስ 90% የአበባና ተክሎች ማብቀል ሥራዎቻቸውን ዘላቂ የማድረግ ፍላጎት ያላቸው የአበባ ማምረት/ አቅርቦት ሰንሰለት ፈር ቀዳጆችን እርስ በርሳቸው አንድ ላይ ያገናኛል። የእነዚህ አብቃይ ኩባንያዎች ቡድንና ባለድርሻ አካላት ዕውቀት ለመጋራትና የዘላቂ ምርትና ንግድ ተጠቃሚ ለመሆን በጋራ ይሠራሉ። አባላቱ እ.ኤ.አ ለ2025 አዲስ ግቦችን አስቀምጠዋል፦