ማኅበራዊ ኃላፊነት

ለገጠር አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ማቅረብ

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ እጥረት አለ። ያም ሆኖ የውሃ ጉድጓዶች በአብዛኛው እጅግ ከፍተኛ ፍሎራይድ ይይዛሉ። እነዚህም ሁለቱን ሥር የሚሰዱ የባዮኬሚካላዊ በሽታዎች የሆኑትን የአጥንት እና/ወይም የጥርስ መበስበስ በሽታዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሰዎች ብዙ ኪሎሜትሮችን በእግር ተጉዘው በአህዮች ውሃ ቀድተው የሚጭኑት በዚህ ምክንያት ነው። ይህ ሥራ በአብዛኛው የሚሠራው በሕፃናት ነው። ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ በዝዋይ ዙሪያ አቅራቢያ ነዋሪ ለሆኑ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ቤተሰቦች ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እያቀረብን እንገኛለን። በቦቼሳና ዎርጃ ዋሽጉላ የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን ወደተለያዩ ቦታዎች በማራዘም በተለያዩ ቦታዎች የውሃ ማከፋፈያ ቦኖዎችን ገንብተናል።

ሼር ኢትዮጵያ ዕድሉን ለተነፈጉ አካባቢዎች ንጹሕ የመጠጥ ውሃ በማቅረብ ለአካባቢው ማኅበረሰቦች ልማት ርዳታ ያደርጋል። ቀጣዩ ፕሮጀክታችን አሉቶ ጉልባ ሆኖ የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን መልሰን በመዘርጋት ሁለት የውሃ ማከፋፈያ ቦኖዎችን እናገናኛለን።

የ8 ልጆች እናትና የቦቼሳ መንደር ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሀሊማ አህመድ በአሁኑ ወቅት የመጠጥ ውሃ ቧንቧ በመኖሪያ ቤታቸው ከገባላቸው ቤተሰቦች መካከል አንዷ ሲሆኑ የመጠጥ ውሃ ለጎረቤቶቻቸው ያከፋፍላሉ። በየዕለቱ የማኅበረሰቡ ዓባላት ጄሪካኖቻቸውን በመጠጥ ውሃ መሙላት ይችላሉ።
ሀሊማ፦ “ሼር ኢትዮጵያ ንጹሕና የመጠጥ ውሃ ማቅረብ ከመጀመሩ በፊት የአካባቢው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ የሐይቅ ውሃ በመጠጣታቸው ምክንያት ይታመሙ ነበር። አሁን በመኖሪያ ቤቴ ቧንቧ መግባቱ በየዕለቱ 2 ኪሎሜትርን በእግር በመጓዝ ውሃ የምንቀዳበትን ጫና አራግፎልኛል። አሁን ልጆቼ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ መጠጣት የሚችሉ ከመሆኑም በተጨማሪ የማኅበረሰቡን የውሃ ቦኖ የመቆጣጠር ሥራ አግኝቻለሁ።”

የመጠጥ ውሃ ስለማቅረብ የተመለከቱ ጠቅላላ አስተያየቶች