ማኅበራዊ ኃላፊነት

የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች

ሼር ኢትዮጵያ በሦስት የተለያዩ ቦታዎች ከ6,500 ለሚበልጡ ሕፃናት ትምህርት ያቀርባል። ለሠራተኞችና ሌሎች የማኅበረሰቡ አባላት ልጆች የአጸደ ሕፃናት፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርትና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚቀርበው በነጻ ነው። ወደ 400 የሚጠጉ ሕፃናት –ከ4 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ – በየዓመቱ በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ተቀባይነት ያገኛሉ። ምዝገባው የሚካሄደው በ50-50 መነሻነት ማለትም ለሠራተኞች ልጆችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ልጆች እኩል ዕድል በመስጠት ነው። በትምህርት ቤት ቅበላ የሚደረግላቸው ተማሪዎች በአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች በሚቋቋም ኮሚቴ ይመረጣሉ።

ሁሉም 1,200 የአፀደ ሕፃናት ተማሪዎች በየዕለቱ ጠዋት ላይ ትኩስ ምግብ በነጻ ይቀርብላቸዋል። 215 መምህራንንና ተጨማሪ 155 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን (አስተዳደር፣ ጽዳት፣ ምግብ ማብሰል፣ ጥገናና ጥበቃ) ቀጥረናል። በዝዋይና አዳሚ ቱሉ የሚገኙት ትምህርት ቤቶች በአብዛኛው ከርትዓዊ ንግድ ከሚገኝ ገንዘብና በሼር ኢትዮጵያ በሚሰጣቸው ገንዘብ ይደገፋሉ። አዳሚ ቱሉ ውስጥ በየዓመቱ ሁለት ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን እንገነባለን።

ሕፃናቱ ምን መማር እንዳለባቸው የሚወሰነው በኢትዮጵያ መንግሥት ነው። የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የመንግሥትን ሥርዓተ ትምህርት ያከብራሉ። ትምህርቱን በእንግሊዝኛ ደረጃዎች መሠረትና በሁለት የአገር ውስጥ ቋንቋዎች፦ አማርኛና ኦሮምኛ እናስተምራለን። ይህ አቀራረብ የትምህርቱን ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ለመጠበቅ ከማገዙም በተጨማሪ በቅርብ አመታት ከዚያም በላይ መሆኑ ተረጋግጧል። ገለለተኛ የመንግሥት ኦዲተሮች እንደ ትምህርት ጥራት፣ አገልግሎት መስጫዎችና በክፍል የተማሪዎች ብዛት በመሳሰሉ መስፈርቶች ላይ ተመሥርተው በትምህርት ቤቶቻችን ላይ የኦዲት ምርመራ ያደርጋሉ። ለብዙ ዓመታት የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ከሚመጣባቸው ትምህርት ቤቶች መካከል አንደኛው ሆነዋል።

ቆቃ ውስጥ ሼር ኢትዮጵያ ለአካባቢው የሕዝብ ትምህርት ቤት ግንባታና አስተዳደር ርዳታ ያደርጋል። ይህ ሦስት የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባትና ተገቢ ዴስኮችን እንዲሁም የመጫወቻ ሜዳ መሣሪያዎችን ለማቅረብ ከስፖንሰሮች ጋር በጋራ መሥራትን ያጠቃልላል። ለደኅንነት/ፀጥታ ዓላማዎች ቅጥር ግቢው ታጥሯል።

የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ጠቅላላ አስተያየቶች