Overview News

አካታች በሆነ መልኩ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8/2024 በሼር ኢትዮጵያ ተከበረ

26 March 2024 Mariska Braam

መጋቢት 8 እና 9 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (IWD) በሼር ኢትዮጵያ ተከበረ. Inspire Inclusion የዚህ ዓመት የአለም አቀፍ ጭብጥ  መርህ ነበር፣ እናም በዚህ መሰረት የተለያዩ የውይይት መድረኮች  ተዘጋጅተውም ነበር።

በዕለቱም መጋቢት 8 በድርጅቱ COO አስዊን ኢንዴማን እና በኦፕሬሽን ዳይሬክተሩ አንድሪው ብሩክ ስሚዝ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ፕሮግራሙ የተከፈተ ሲሆን በንግግራቸውም ላይ ሁሉንም ሰራተኞች ላይ በእኩል፣  በንቃት ሲሰራበት እና የሁሉንም ባልደረቦችንን አስተዋፅኦ ስንመለከት ለኩባንያው መሳካት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል።።

ከዚያ በኋላ የሥርዓተ-ፆታ ኮሚቴው በኔዘርላንድ ውስጥ በምትገኝ ዞተርዎዴ ከተማ ምክር ቤት ሴቶች ጋር በበይነ መረብ ስብሰባ በማድረግ በአንድ ላይ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እያከበሩ ነበር፣ በዛም ተያይዞ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እና እርስ በእርስ ለመማማር አበረታች መንገድም አግኝተው ነበር።

መጋቢት 9 ከሁሉም ሰራተኞቻችን ጋር በመሆን በድጋሚ IWD በእርሻችን ላይ አክብረንም ነበር። ይህም በዝዋይ እርሻ ላይ በመግቢያው በር ላይ የፎቶ መነሻ ቦርድ   የተዘጋጀ ሲሆን የስርዓተ-ፆታ ኮሚቴውም ሰራተኞችን በሙዚቃ እና በዳንስ ሲቀበል ነበር በዚህም መርሃ ግብር ውስጥ ብዙ ፎቶግራፎች የተወሰዱ ሲሆን ለብዙዎችም ቀኑ ጥሩ እና አስደሳች የሆነ የስራ ቀንም ነበር።

ወደ ሼር ኢትዮጵያ ለስራ የሚመጣ ሰራተኛ ሁሉ ስለግል ንፅህና ምቾት እንዲሰማው እና አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት መስጠት ይፈልጋል፣ በዚህ ምክንያት ኩባንያው ‘Mela for her’ መላ ለእርሷ የሚባል እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እሽጎችን በሁሉም እርሻዎች ላይ ለአበባ ቆራጮች አከፋፍሏል። እንዲሁም በቀጣይ ለሌላ ክፍል ሴት ሰራተኞችም እንዲሁ የሚደርስ ይሆናል።

በመጨረሻም በዝዋይ እርሻ በሚገኘው መዝናኛ አዳራሽ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ኮሚቴው ከሴቶች መብት፣ ከሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ ከሴቶች በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶችና ስኬቶች የሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

በኩባንያው ውስጥ የሴቶችን ስኬት ያከበርንበት እና አካታች ስራንም ለመስራት ያነሳሳንበትን ታላቅ ቀን መለስ ብለን ስንመለከትም መሪ ቃሉን ‘Invest in women እድገትን ለማፋጠን ይረዳል’ መማለት ሁላችንም ይህንን እንድናስታውስ እና ቀን ከቀን የስራችን አንዱ አካል ልናደርገውም ይገባናል።