ማኅበራዊ ኃላፊነት

ስፖርትና የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ

Sher Ethiopia's outdoor sports field with players
ስፖርት

ሼር ኢትዮጵያ የራሱ የመስክ ላይ የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄዱበት ስታዲየም ያለው ሲሆን በስታዲየሙ የእግር ኳስና መረብ ኳስ ውድድሮችን እናካሂዳለን። ከራሳችን የውስጥ ውድድሮች በተጨማሪ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚዘጋጁ ውድድሮችን እናስተናግዳለን። ከዚህ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ታዋቂ አገር አቀፍ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የቡና ቡድንን በኛ ሜዳ እንዲጫወት ለማድረግ በመቻላችን ደስተኞች ነን።

የክበብ አዳራሽ

የሼር ኢትዮጵያ ክበብ አዳራሽ ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውል ሕንጻ ሲሆን ለስብሰባዎች፣ የሠርግ ዝግጅቶች፣ ፓርቲዎችና ትዕይንቶች ጥቅም ላይ ይውላል። የክበብ አዳራሹ ለሠራተኞች ዝግጅቶች ያለ ምንም ክፍያ ግልጋሎት ላይ ሊውል ይችላል።