አማን ቃሲም / የዝዋይ የሼር ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመርኩት በ2013 (2005 ዓ.ም.) ነው።
እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
ትምህርት ቤቱ ውስጥ የተቀጠርኩት በመምህርነት የነበረ ሲሆን ለሦስት ዓመታትም አስተምሬያለሁ። ከዚያም የደረጃ ዕድገት አገኘሁና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ሆንኩ።
ሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
በጣም ጥሩ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤቱ ወደ 6,500 የሚጠጉ ተማሪዎችን በነጻ ከማስተማሩ በተጨማሪ በየዕለቱ 1200 ሕፃናትን ይመግባል። ይህ በእጅጉ የሚያኮራ ከመሆኑም በላይ ደመወዜ ደግሞ በወቅቱ ይከፈለኛል። በዚህና በሌሎችም ያልገለጽኳቸው ምክንያቶች የተነሣ በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ውስጥ መሥራቴ ያስደስተኛል።
ሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ውስጥ ሌሎች ሰዎች እንዲቀጠሩ ለምን ይመክሯቸዋል?
በጣም ጥሩ መምህራንና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስላሉን ክፍት ሥራ ማስታወቂያ ሲወጣ ለመቀጠር እንዲወዳደሩ ሌሎች ሰዎችን አጥብቄ እመክራለሁ።
ሲስተር መስከረም ክብሩ/ የጤና መኮንን
በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የተቀጠርኩት በ2007 (1999 ዓ.ም.) ነው።
እባክዎ በምን ዓይነት የሥራ ዕድገትዎ ምን እንደሚመስል ይግለጹልን
መጀመሪያ ሥራ ስጀምር ነርስ ነበርኩ በኋላ ላይ ወደ ጤና መኮንንነት አደግኩ።
ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል ውስጥ ተቀጥሮ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
ሆስፒታሉ የተለያዩ መምሪያዎች፣ ጥሩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና በጣም ቀና የሆኑ የሥራ ባልደረቦች የሚገኙበት በጣም ጥሩና ትልቅ ሆስፒታል ነው። ሆስፒታሉ ለኔ ሙያ የሚያስፈልጉት ነገሮች በሙሉ አሉት።
ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
በምናቀርባቸው የተለያዩ አገልግሎቶች የተነሣ ሼር ኢትዮጵያ ለአቅርቦቶችና መሣሪያዎች መዋዕለ ንዋይ ይከፍላል። ከሌሎች ሆስፒታሎች አንጻር ይህ ልዩ ነው። ስለሆነም ክፍት የሥራ መደብ በሚኖርበት ጊዜ ሁሉ ለጓደኞቼ እንዲያመለክቱ እመክራቸዋለሁ።