የሥነ ምግባር ደንብ ለአበባ እርሻ
በአበባ እርሻ ዘርፉ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው ኃላፊነት የሚሰማው የንግድ ሥራ ሥነ ምግባር ደንብ ስምምነት ፈራሚዎች እንደመሆናችን የ IRBC የአበባ እርሻ የሥነ ምግባር ደንብን ተቀብለን በሥራ ላይ አውለናል። ይህ ደንብ የንግድ ሥራ ሥነ ምግባር 12 መርሆዎችን ይደነግጋል። ይህ ጽሑፍ የሥነ ምግባር ደንቡን በአጭሩ አጠቃሎ በማቅረብ ደንቡ ሊነሡ ለሚችሉ ሥጋቶች ጥናት በምን መልኩ እንደ ጠቃሚ የመነሻ ነጥብ ሊሆን እንደሚችልና ተገቢነት ያለው ትጋትን የተላበሰ አሠራር እንዲኖር እንዴት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል ያብራራል። መርሆዎቹ (OECD እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) መመሪያዎችን፣ ሕግንና ማረጋገጫዎችን ጨምሮ) አሁን ባሉት የዘላቂነት መስፈርቶች ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ ተገቢነት በሚኖረው ወቅት በአበባ አምራች ዘርፉ ላይ ተደንግገው ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።