በቅርቡ ትልቅ እድሳት የተደረገለት የጥርስ ክሊኒኩ፣ አሁን ላይ ሁለት የጥርስ ህክምናን መስጫ ወንበሮች ያሉት ሲሆን ይህም የህክምና ሂደቱን የበለጠ ውጤታማ ሊያደርገው ችሏል ። በተጨማሪም ዘመናዊ ያልነበርዉ የኤክስሬይ ማሽን በተንቀሳቃሽ ዲጂታል ኤክስሬይ ማሽን በመተካቱም ፊልም ከመጠቀም ይልቅ ፎቶ ለማንሳት ኤሌክትሮኒክ የሆነ ዘዴን እንድንጠቀም አስችሎናል።
ከዚህ ቀደም የነበረው የኤክስሬይ ቴክኖሎጂን ስንጠቀም ኬሚካሎች ያስፈልጉ ነበር. ከዚህም በላይ ብዙ ጊዜም ይ ወስዷል ስለሆነም የምስሎቹ ጥራት ከዲጂታል ኤክስሬይ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛም ነበር። ለዚህም ነው ተንቀሳቃሽ ዲጂታል ኤክስሬይ ማሽን መግዛት ያስፈለገው።
የክፍሉ የጥርስ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ነጻነት አበበ ፡ ”በክሊኒካችን ውስጥ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል ኤክስሬይ ማሽን በመጨመሩ በጣም ደስተኛ ነኝ ፣ ዲጂታል ኤክስሬይ ማሽኑ የታካሚዎቻችንን ፍሰት የበለጠ ቀልጣፋ በማድረግ ና ተፈላጊዉን የታካሚዎቻችንን የጥርስ ክፍል ለማየት ያስችለናል ሲሉም አክለዋል”።
ሼር ኢትዮጵያ ለሰራተኛው፣ ለሼር-ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ለማህበረሰብ አባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ባለው ሆስፒታሉ ላይ ኢንቨስት ማድረጉን ይቀጥላል።.