ዘላቂነት

የቆሻሻ አወጋገድ

waste_management
መለየትና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል

ደረቅ ቆሻሻ

በሚቻልበት ጊዜ ሁሉ ቁሳቁሶችን መልሰን ጥቅም ላይ ለማዋል እንሞክራለን። ለምሳሌ፦ ያረጁ የግሪንሀውስ የፕላስቲክ ሽፋኖች ተቆራርጠው በግሪን ሀውሶች ውስጥ ለሚሰበሰቡ የፅጌረዳ አበባዎች መያዣና መከላከያ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ያረጁ የመስኖ ቱቦዎች ለፅጌሬዳ አበባ መደቦች መከላከያ ለመሥራት ቋሚ/ምሶሶ ሆነው ያገለግላሉ።

ቁሳቁሶች የአገልግሎት ዘመናቸው ማብቂያ ላይ ሲደርሱ ከመሸጣችን ወይም ለአካባቢው ማኅበረሰብ የመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አካላት ከመስጠታችን በፊት እንለያቸዋለን። ይህ ካልሆነም ይወገዳሉ። ይህ በክልሉ ውስጥ ዘላቂነትን ለማስቀጠል ያስችለናል።

ፈሳሽ ቆሻሻ

ሁሉም ፈሳሽ ቆሻሻ በበሰው ሠራሽ ረግረግ ውስጥ ይታከማል።