ዘላቂነት

የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር

employees_pest_management

ፅጌሬዳ በምናበቅልት ጊዜ የተባይና በሽታዎች ክስተት አይቀሬ ነው። ሆኖም እነዚህን በሽታዎችና ተባዮችን መቆጣጠር የማይቻል አይደለም። ሼር ኢትዮጵያ የተፈጥሮና ከኬሚካል ነጻ የሆነ የተባዮች መቆጠሪያ ዘዴዎች በላቀ መልኩ ይጠቀማል። የሰዎችንና የአካባቢ ጤናን ማሻሻል አስፈላጊ ግብ ነው። በተቻለ መጠን ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ወይም ከኬሚካል ነጻ በሆኑ ውህዶች መሥራትና የኬሚካል ምርቶችን ጥቅም ላይ ማዋልን መቀነስ ቀጣይ ምኞታችን ነው።

ፅጌሬዳ አበባዎቻችን በቀጣይነት ተገቢ ሥልጠና በወሰዱ ሠራተኞች፣ “ስካውቶቻችን” ምርመራ ይደረግባቸዋል። ይሄም የሚደረገው የፅጌሬዳ ተክሎቹ ከተባይ ነጻ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ነው። ስካውቶቹ በተጨማሪም በቂ በሕይወት ያሉ ጠቃሚ ነፍሳቶች መኖራቸውን ወይም ከሌሉ ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግ ስለ መሆኑ ያረጋግጣሉ። የተወሰኑ ነፍሳቶችን መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚያጣብቁ ወጥመዶች ጥቅም ላይ በማዋል የተባይ ህላዌንና በምን ያክል መጠን ስለመኖራቸው የሚደረግ ግምገማ ሥራን ቀላል እንዲሆን ያደርጋል።

የተባይ የተፈጥሮ ጠላቶችን መጠቀም፦ የተቀናጀ የተባይ ቁጥጥር (IPM)

የ IPM ሥራ ጤናማ የሆነ ተክልን በመትከል ይጀምራል። የተክል ማሻሻያዎችን የምንጠቀመው ለዚህ ነው። እነዚህ ንጥረ ነገሮች የተክሉን ዕድገት ያጠናክራሉ፣ የአበባውን ሥር ውስጠ ሥርዓትና አካባቢውን ያፋፋሉ፣ የአፈር ሁኔታዎችን ያሻሽላሉ እንዲሁም ጤናማ ሥርዓተ ሕይወት እንዲኖር ያደርጋሉ። ይህም የተፈጥሮ ሂደቶችን ዑደት ያነቃቃል። የተክሉ በሽታንና ተባይን የመቋቋም አቅም ከፍ ስለሚያደርገው ጤናማ ተክሎችን በመጨረሻ ለማግኘት ያስችላል። ጤናማ ተክል ለተባይና በሽታዎች ተጋላጭነቱ አነስተኛ በመሆኑ ተባይና በሽታዎች የሚያጋጥሙበት ዕድልም ያነሰ ይሆናል።

በግሪን ሀውስ ውስጥ ተባይ የሚገኝ ከሆነ በተቻለ መጠን የተባዩ የተፈጥሮ ጠላት ልክ እንደ የተባይ መቆጣጠሪያ ኤጀንት/ ዘዴ ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ ለትናንሽ ሸረሪቶች የተፈጥሮ ጠላት አዳኝ ሸረሪት ይሆናል። የተፈጥሮ የተባይ መቆጣጠሪያ ምርቶች በፅጌሬዳ አበባዎቹ ላይ እንዲበተኑ ይደረጋል። እነዚህ ህያው መከላከያ ዘዴዎች በትናንሽ ብልቃጦች ተደርገው የሚመጡ ነፍሳት ሲሆኑ የተራባውን ተባይ በተፈጥሯዊ አኳኋን ለመቆጣጠር ያስችላሉ።

employee_in_picking_roses_greenhouse

ከነፍሳቶች በተጨማሪ አንዳንድ በሽታዎች በፈንገስና ሻጋታዎች ምክንያት ሊመጡ ይችላሉ። በርግጥ ባለ ስስ ላባ ሻጋታና ዱቄታማ ሻጋታ ሁለቱም በመደበኛነት የሚያጋጥሙ ሻጋታዎች ናቸው። የIPM ቴክኒኮችን፣ የሰብል ቁጥጥር እርምጃዎችን በመተግበር፣ የተፈጥሮ የመቋቋም አቅምን በማሳደግና ውጤታማ በሆነ መልኩ የተለያዩ ዝርያዎችን በመምረጥ የፅጌሬዳ አበባዎችን ለእነዚህ በሽታዎች ተጋላጭነታቸውን ማሳነስ ይቻላል። ከእነዚህ ዘዴዎች በተጨማሪ ከኬሚካልና ከኬሚካል ነጻ የተባይ መቆጣጠሪያ ኤጀንቶችን መጠቀም አስፈላጊ ነው። እነዚህ የአበባ እንክብካቤ ሥራዎች የሚሠሩት በጥብቅ የደኅንነት መጠበቂያ እርምጃ አወሳሰድ ዘዴ በሠለጠኑ ሠራተኞች ሲሆን የመከላከያ አልባሳትንና የፊት ጭምብሎችን መጠቀምን ያስገድዳል።

ምንም እንኳን በተቻለ መጠን የምንጠቀመው የተፈጥሮ ጠላቶችን ቢሆንም በሁሉም ሁኔታዎች ላይ ይህን ዘዴ ብቻ መጠቀም የሚያዋጣ አይደለም። የኬሚካልና ከኬሚካል ነጻ መቆጣጠሪያዎች ሁልጊዜ አስፈላጊ ናቸው። ለምሳሌ ጎጂ ነፍሳትን ሳሙናማ ውህዶችን በመርጨት መቆጣጠር ይቻላል። ይህ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ውጤታማ ቴክኒክ ነው።

ጥብቅ መስፈርቶች

ለአካባቢ ጎጂ የሆኑ ወይም ምን ዓይነት ተፅዕኖ ሊኖራቸው እንደሚችል በትክክል ያልታወቀ ምርቶች ጥቅም ላይ አይውሉም። ይህ የሚደረገው የሠራተኞቻችንንና የአካባቢን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ነው። በአካባቢ ወይም በእርሻዎቻችን የሥራ ሁኔታዎች ላይ ምንም አሉታዊ ተፅዕኖ ሳናደርስ ለደንበኞቻችን ተመራጭ የጥራት ደረጃ ያላቸው የፅጌሬዳ አበባዎችን ለማቅረብ የተቀመጡትን መስፈርቶች በጥብቅ እናከብራለን። የአሠራር ዘዴዎቻችን በቋሚነት በተለያዩ የውጭ ድርጅቶች አማካይነት ምርመራ ይደረግባቸዋል። ጥቅም ላይ የሚውሉት የተባይ መቆጣጠሪያ ኤጀንቶች ብዛትና ዓይነት በተከታታይ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችንና የደንበኞቻችንና ማኅበረሰብ ምርጫዎችን እንደ መለኪያ ካስማ አድርጎ ይጠቀማል።

ቀጣይነት ያለው የተፈጥሮ የተባይ መቆጣጠሪያዎችና ከኬሚካል ነጻ ምርቶችን መፈለግና መጠቀም ሼር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን በዘርፉ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ድርጅት እንዲሆን አስችሎታል።

Pest_management