በሼር ኢትዮጵያ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰራተኞችን ማካተት የተለመድ ተግባር ነው። ስለዚህም በፌይርትሬድ አፍሪካ ዶናት ፕሮግራም ውስጥ በቁጥር 70 የሚሆኑ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች ይበልጥ ምቹ በሆነ መንገድ ስራቸውን እንዲሠሩ ሊረዳ የሚያስችሏቸው የአካል ድጋፍ መስጫ መሣሪያዎች ተበርክቶላቸዋል ለዚህም ምስጋናችን ከልብ ነው።
የመጀመሪያውን ዙር ጨምሮ በጠቅላላው 178 ሰራተኞች ከዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
በዚህ ፕሮጀክት ሼር ኢትዮጵያ እና ፌርትሬድ አፍሪካ በዝዋይ ከሚገኘው ከግራርቤት የተሃድሶ ማህበር ጋር በመተባበር ተጠቃሚዎቹ ምን ምን አይነት መሳሪያ እንደሚያስፈልና የሚያስፈልጉትንም የመሳሪያዎቹ ትክክለኛነትና ተስማሚነት ለመወሰን ልኬት እንዲፈፅሙ ይደረጋል። ከእነዚህም መካከል ባለ ሦስት ብስክሌቶች፣ ምርኩዝ፣ ሰው ሠራሽ እጅና መነጽር እንዲሁም መስማትን የሚያግዙ መሣሪያዎች ይገኙበታል።
ፌይርትሬድ አፍሪካ እና ግራርቤት የተሃድሶ ማህበር ላከናወኑት ታላቅ ስራ እና ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን