በባቱ /ዝዋይ የሚገኘውን የሼር ሆስፒታል አገልግሎቱን ለማሻሻል ባደረግነው ጥረት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆነ BS-200E ኬሚስትሪ ማሽን ለመግዛት ከደች ፍላዎር ፋውንዴሽን ከፍተኛ ልገሳ አግኝተናል። ይህ መሣሪያ ብዙ አይነት ሪኤጀንቶችን መጠቀም የሚያስችል ያልተገደበ አሰራልን የያዘ ነው ስለሆነም ሆስፒታሉ በጥሩ ዋጋና ጥራት የተለያዩ የሪኤጀንት ዓይነቶችን ከገበያ በመግዛት አገልግሎቱን እንዲሰጥ ያስችለዋል ።
የላቦራቶሪ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ሱራፌል ከበደ እንደተናገሩት ምርመራን በአፋጣኝ ለማከናወን ብቃት ያላቸው ሠራተኞች ብቻ ሳይሆኑ ዘመናዊ የሆኑ የላቦራቶሪ ማሽኖች ሲሟሉ ስርአቱ ወይም ደንቡ የሚጠይቀውን ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠትን እንደሚያስችል ይገልፃሉ። ላቦራቶሪ ክፍሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ክፍሎችን በማስፋፋትን፣ ነባር መሣሪያዎችን በአዲስ በመተካት እና ሠራተኞችንም የማሠልጠን ፕሮግራሞችን ጨምሮ ታላላቅ ማሻሻያዎችን አድርጓል። አዲሱ የኬሚስትሪ መመርመሪያ ማሽንም አገልግሎታችንን ይበልጥ ለማሻሻል ይረዳናል ሲሉ ፣ አክለውም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የሼር ሆስፒታል ሠራተኞች የሁል ጊዜ ተባባሪያቸው የሆነውን የደች ፍላወር ፋውንዴሽንን አመስግነዋል።
በሼር ሆስፒታል ውስጥ ሁሉም የሼር ሰራተኞች ( 12.500 የሚጠጉ) እና የሼር-ተማሪዎች (6.500 የሚሆኑ) ነፃ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ። እንዲሁም የህብረተሰቡ አባላት በአነስተኛ ወጪ ይገለገላሉ። በየዓመቱ ከ100.000 የሚበልጡ ታካሚዎች በሆስፒታሉ ሕክምና ይደረግላቸዋሉ።
የደች አበባ ፋውንዴሽን (DFF) አላማውም የተቸገሩ ሰዎችን በተለይም ህፃናትን የኑሮ ሁኔታ እና ደህንነት ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል።