Overview News

ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለሌላ አራት ተማሪዎች ተሰጠ

20 March 2023 Aswin Endeman
Awarded Barnhorn Scholarships to 4 students

በቅርቡ ለሁለተኛ ዙር ጌሪት እና ኔል ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለአራት የሼር-ትምህርት ቤት ተማሪዎቸ ተሰጥቷል። የባርንሆርን ቤተሰብ ሼር ኢትዮጵያ  እርሻን ፣ ሆስፒታል ና ትምህርት ቤቶቹን የመሰረቱ ናቸው። በየአመቱ ለ4 ተማሪዎች በኢትዮጵያ በመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ወጪን እና የኑሮ ውድነት ለመደገፈ ብሎም ለመሸፈን የሚረዳ ወርሃዊ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። የስኮላርሺፑ ዋና ግብ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡና  የተቸገሩ ተማሪዎችን ለመርዳት ያስበ ነው።

ተማሪዎቹም ጣሃ አቡ ጁላ፣ ተመስገን ሰለሞን ስጦታ፣ ደጀኔ ኢጃሮ ናኔሶ እና ሃና በላይሁን ድልነሳው ሲባሉ ሽልማታቸውን ከጌሪት እና ኔል ባርንሆርን ልጅ ከጆን ባርንሆርን እጅ ተቀብለዋል። ጆን ባርንሆርም ተማሪዎቹ ላለፉት 16 ዓመታት ላሳዩት ትጋት  እና እንዲሁም የሼር ትምህርት ቤት መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በተማሪዉ ቤተሰብ ስም አመስግኗል።

ከሁሉም 12 ከፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎቸ ዉስጥ 8 ተማሪዎች  ለስኮላርሺፕ  ታጭተው 4ቱ በመጭረሻዉ ማጣሪያ ተመርጠዋል። ሌሎቹ 4 ቶቹ ድገሞ  እያነዳነዳችዉ የላፕቶፕ ሽልማት አግኝተዋል። ስነ ስርዓቱም የተማሪ ቤተሰቦች፣የሼር ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጆች፣የማህበረሰብ ሽማግሌዎች፣የሼር ት/ቤት ሰራተኞች፣የወላጆች ኮሚቴ እና የትምህርት ጽ/ቤት  አስተዳደሮች ፣ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሼር ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ  ተካሂዷል።

አቶ  ባርንሆርን እና ቤተሰባችው ባለፉት አመታት ለሼር ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታል ያላሰለሰ ድጋፍ ስላደረጉልን እያመሰገንን እነዚህ ተማሪዎች ሼር ኢትዮጵያ በዝዋይ እና አካባቢው ማህበረሰብ ላይ እያሳደረ ያለው አዎንታዊ ተጽእኖ እውነተኛ ምሳሌ መሆናቸው ለመግለፅ እንወዳልን። ሁሉም የ12ኛ ከፍል ፈተናን ላጠናቀቁ ተማሪዎቸ እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎቸ ለተመደባቸዉ ተማሪዎች  መልካም የተምህርት ጊዜን እንመኘላችሃልን።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሼር ትምህርት ቤቶች ከ6800 በላይ ተማሪዎችን በሶስት ቦታዎች ያስተምራሉ። ወደ 400 የሚጠጉ ህጻናት – ከ 4 አመት ጀምሮ – በየዓመቱ በሼር ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ወይም ቅበላ የሚከናወን ሲሆን ይህም 50 %  ከአካባቢው ማህበረሰብ  ልጆች  እና 50% ቱ ድገሞ ከሠራተኞች ልጆች  ይሆናለ።