Overview News

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የተደረገ የምግብ እርዳታ

7 October 2022 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ የእርዳታ ተጠቃሚዎች

ባለፈው አንድ አመት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ  እንዲሁም የወደሙ ሰብሎች እና ለሞት የተዳረጉ እንስሳት እንዳሉ አንዳንድ መረጃዎች  ይጠቁማሉ። በዝዋይ እንዲሁም በአዳሜ ቱሉ ዙሪያ ከተጎዱ አካባቢዎች ዉስጥ የተወሰኑትን ለመደገፍ ያህል ሼር ኢትዮጵያ ወደ 800 ለሚጠጉ አባወራዎችን ለእያንዳንዳቸዉ 25 ኪሎ ግራም የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል። ይህንንም በሼር ኢትዮጵያ ማኔጅመንት ስም ለአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ አስተዳደር አስረክቧል። ስርጭቱም በተመሳሳይ የርክክቡ እለት መካሄዱን የድርጅቱ የህዝብ  ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አማን ሙዳ ገልጸዋል።

የሼር ኢትዮጵያ የእርዳታ ቡድን የሼር ኢትዮጵያ የእርዳታ ማደያ ጣቢያ የሼር ኢትዮጵያ የእርዳታ ተጠቃሚዎች የሼር ኢትዮጵያ የእርዳታ ስርጭት ሂደት የሼር ኢትዮጵያ የእርዳታ ዕቃዎች ክምችት የሼር ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ስርጭት