Overview News

የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ

9 August 2023 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ቡድን

የአየር ንብረት ለውጥን እና የደን ጭፍጨፋን ለመግታት ያቀደው አረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ቀድም ሲል በሀገሪቱ ከ6 ዕመታት በፊት የተጀመረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላው ኢትዮጵያ 3.7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንደተተከሉ ይነገራል።. በዚህም መሰረት በየዓመቱ ለዘመቻው አስተዋፅኦ  የምናደርግ ሲሆን በዚህም ዕመት በሐምሌ ወር የሥራ ባልደረቦቻችን በወርጃ እና በቃሞ ገርቢ ጋራዎች ላይ ከ 46.000 በላይ ችግኞችን በመትከል ተሳትፈዋል፣ ይህንንም በአከባቢው የአስተዳደር ጽ/ቤት ፣ በአከባቢው ባለሀብቶች እና በማህበረሰቡ ትልቅ ትብብር ማሳካት ተችሏል።

በተጠበቁ አካባቢዎች ችግኞችን ከመትከል በተጨማሪ በ 4ቱ የሼር ት/ቤቶችም ጊቢ ውስጥ 300 የፍራፍሬ ተሸካሚ ዛፎችን እና 1.000 ሌሎች ችግኞችን ተክለናል። በጥቅሉ በዘመቻው የተሳተፉትን የሥራ ባልደረቦቻችን እና በጎ ፈቃደኞችን ሁሉ ለማመስገን እንወዳለን።

የሼር ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ቡድን የሼር ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሳታፊዎች የሼር ኢትዮጵያ የዛፍ ትከላ ዝግጅት የሼር ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ