ባሳለፍነው ሳምንትበሼር-ትምህርት ቤታችን ለሚገኙ ለ1300 ሴት ተማሪዎች ፡ መላ ለሷ የሚል መጠሪያ ያለው አዲስ ፕሮጀክት ጀምረናል። የፕሮጀክቱ መጠሪያም እንዲሆን የመረጥነው (መላ)የአማርኛ ትርጓሜያዊ ፍች መፍትሄ የሚል ትርጉም ኣለው። በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ለብዙ ወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶችችግር የሆነውን በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነየሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች እጥረትየሚቀርፍ መፍትሄ ነው:
ለብዙ ሰዎች የወር አበባ ንፅህና ጥበቃ ምቹ አይደለም። በዓለም ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጃገረዶች ደግሞ በትምህርት፣ በጤና፣ በራስ መተማመን እና በሰብዓዊ መብቶቻቸው ላይ እንቅፋት ይፈጥራል። ለሌሎች ብዙዎች ደግሞ የወር አበባ መጀመር ለትምህርትመስተጓጎል ምክንያት ሲሆን ይታያል።
መላ ለእሷ፥ለአካባቢ ተስማሚ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የወር አበባ ምርቶችን እና የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ትምህርትን በመስጠት፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ህይወት ለመለወጥ ወጥኖ የተነሳ ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ ድርጅት ነው። የሼር ትምህርት ቤቶች እና መላ ለእሷትብብር እና በኔዘርላንድ የአበባ ፋውንዴሽን እርዳታ እድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ዓመት ላሉ 1300 ልጃገረዶች፥የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያዎችን እርዳታ እናቀርባለን። ከንፅህና መጠበቂያዎቹ በተጨማሪ የባለሙያዎች ቡድን የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን የሚያሰለጥን ሲሆን፣ ለ1300 ተማሪዎች ደግሞ በሴቶች ክበብ በኩል የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ላይ ስልጠና ይሰጣል።
የመላለእሷ ቡድን ላደረጉት ትብብር ትልቅ የሆነ ምስጋና እናቀርባለን ፥በመቀጠል የሆላንድ አበባ ፋውንዴሽን ለዚህ ተግባር ላደረጉት ድጋፍ እና ለወደፊትምለዚህ ፕሮጀክት ቀጣይነት ያለው ድጋፍለማድረግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን። ወጣት ሴቶች እምቅ ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ ክብራቸው የሚጠበቅበት መብታቸውንም የማይጣስበት ዓለም አንድ ላይ እንገንባ።