Overview News

ሼር ኢትዮጵያ አዲስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዳሚ ቱሉ ከፈተ

11 December 2023 Aswin Endeman

በህዳር ወር በቀን 11 ሼር ኢትዮጵያ በአዳሚ ቱሉ አዲስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፈተ። የመክፈቻ ስነስረዕቱም በፕሮገራሙ ላይ ተጋብዘው በነበሩ እንግዶች የተከበሩ አቶ ኡስማን ቱሴ የባቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ ፣ አቶ ከዲር ጀቤሶ የባቱ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ፣ ሚስተር አስዊን ኢንድማን የሼር ኢትዮጵያ የቢዝነስ ድጋፍና ሲኤስአር ስራ አስኪያጅ እንዲሁም አዳሚ ቱሉ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ሽማግሌዎች፣ የሼር ኢትዮጵያ አስተዳደር ተወካዮች፣ መምህራን እና በአጠቃላይ ቁጥራቸዉ 192 የሚደርሱ ተማሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።

ትምህርትን ከክፍያ ነፃ መስጠት የሼር ኢትዮጵያ ዋና እሴት ነው. እ.ኤ.አ. በ 2017 ተጀምሮ የነበረው የሁለተኛው እርሻ ግንባታ በአዳሚ ቱሉ በመጠናቀቁ ድርጅቱ በከተማዉ ውስጥ ባሉ አዳዲስ የትምህርት ቤቶች ላይ ኢንቨስት አያደረገ ይገኛል። በ2019 ሼር መዋዕለህፃናቱን በመክፈት የጀመረው ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት 342 ተማሪዎችን ይዞ በማስተማር ላይ ይገኛል። ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላም የመጀመሪያዎቹ የተማሪዎች ማለትም ቁጥራቸው ከላይ የተጠቀሰው በአሁኑ ወቅት በ አዲሱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በመማር ላይ ላይገኛሉ። ሁለቱ ትምህርት ቤቶች በመካከላቸዉ የ500 ሜትር ያህል ርቀት አላቸው።

ሼር በየአመቱ 4 አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት ያቀደ ሲሆን፣ ይህ አዲስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ8 ዓመታት ውስጥ ወደ 1500 የሚጠጉ ተማሪዎች ያይዛል ግቢውም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመጨመር በቂ ነው።

የሸር ትምህርት ቤቶች ከሼር ሰራተኞች ለመጡ ልጆች እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመጡ ልጆች አቅም በፈቀደ ሁሉ ክፍት ናቸው።

ይህንን አዲስ ትምህርት ቤት እውን ለማድረግ ለረዱ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው። ከራሳችን የግንባታ ቡድን እስከ ሲቪል ሰርቫንቶች፣ ከመምህራን እስከ ጽዳት ሠራተኞች ድረስ ለሁሉም ምስጋናችን ይድረሳቸው።

ይህ ትምህርት ቤት ለአዳሚ ቱሉ ማህበረሰብ የአንድነት፣ የእድገት እና የዘላቂ መንፈስ ምልክት ይሁን እያልን ብዙዎች የሚማሩበት እና የእውቀት ነበልባል ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው ትውልድ የሚተላለፍበት ቦታ ይሁን ዘንድ ምኞታችን ነው።