በ2015 አዲስ ዓመት በወረሃ መስከረም የሼር ኢትዮጵያ ፕሪሚየም ኮሚቴ በባቱ /ዝዋይ/ ከተማ የሚገኙ አሮጌ እና እጅግ ተበሳቁለዉ የነበሩ16 የመኖሪያ ክፍሎች አፍርሶ እንደ አዲስ በመገንባት ከዚያም ቀደም ሲል በአሮጌዉና እጅጉን በተበሳቆለዉ ቤት ዉስጥ ሲኖሩ ለነበሩት ነዋሪዎች አስረክቧል፡፡ ከ 16 መኖሪያ ቤቶቹ ባሻገር የጋራ የሆኑ 2 ኩሽና እና 6 የወንድ አና የሴት መታጠቢያ ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎቹ ተሰጥተዋል፡፡ይህም ፕሮጀክት ተጀምሮ የነበረዉ ከዛሬ 18 ወር አካባቢ ሲሆን በሼር ፌርትሬድ ፕሪሚየም ኮሚቴ ከፌርትሬድ አበቦች ሽያጭ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተሰራ ሲሆን ፣ እነዚህም 16ቱ የመኖሪያ ክፍሎች አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ያካተተ ሲሆን ለነዚህም ነዋሪዎች ጥሩ መኖሪያ ቤት እና ንፁህ የንፅህና መጠበቂያ ክፍሎች በማሟላት ጤናማ የመኖሪያ አካባቢ እንዲኖራቸዉ አድጓል።
ሼር ኢትዮጵያም እንደ አንድ አጋር ድርጅት የሁሉንም የጉልበት እና የሙያ ሰራተኞችን ወጪ በመሸፈን ለፕሮጀክቱ መሳካት የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። የቤቶቹ የርክክብ ሂደትም የባቱ /ዝዋይ/ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የፌርትሬድ አፍሪካ ተወካይ አቶ ቦኒፌስ ሉዋንዳ በተገኙበት ለነባር ነዋሪዎች ተላልፈዋል። ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ኮሚቴዉን እና ለሌሎች አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በጠቅላላ ላቅ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።