Overview News

ለ IGA የሚሰጥ ድጋፍ፦ ንብ ማንባትና ሥነ ምኅዳርን የጠበቀ ቱሪዝም አገልግሎት

10 July 2022 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ የህብረተሰብ ግንኙነት ስብሰባ

አፍሪፍሎራና ሼር ሥራቸውን በሚያከናውኑባቸው አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ ማኅበረሰቦችን ለማጠናከር እንዲቻል ከራሳቸው ከማኅበረሰቦቹ ለተውጣጡ ቡድኖች የተለያዩ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ እንቅስቃሴ የሚደረጉባቸውን በርካታ ፕሮጄክቶች ድጋፍ ይሰጣሉ። ባለፉት ወራት ብቻ በርካታ ቡድኖች በንብ ማንባትና ሥነ ምኅደርን የጠበቀ ቱሪዝም አገልግሎት ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል።

ከ 4 እስከ 10 አባላት ላሏቸው 13 ቡድኖች 50 የንብ ቀፎዎች ተከፋፍለዋል። በድምሩ 80 ሰዎች ስለ ማር ምርት አመራረት መሠረታዊ ዕውቀት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል። ከእያንዳንዱ የነዚህ ፕሮጄክት አባል የሆነ ሰው ጀርባ ተጠቃሚ የሆኑ ብዙ ቤተሰቦች አሉ። እዚህ ላይ እንደ አብነት ለመጥቀስ ያህል፣ ሙስጠፋ አቡ ንዑስ ቡድን/አፒያሪ የተባለው (ፎቶ ላይ የሚታየው) ቡድን ነው። የዚህ ቡድን አባላት በማር ምርት ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን ማር ሸጠው ከሚያገኙት ገንዘብ አብዛኛውን ተጨማሪ የንብ ቀፎ ለመግዛት ሊጠቀምበት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። አንድ ላይ ተባብሮ በመሥራት አንድን ቤተሰብ ብቻ ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ መላው ማኅበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል። ከምርቱ የተወሰነው ክፍል ራሳቸው አማራቾቹ የሚጠቀሙበትም ይሆናል።

ከወርጃ ዋሽጉላ እና ካሞ ገርቢ አካባቢ የመጡ ሥነ ምኅደርን በጠበቀው ፕሮጄክት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ 20 ተጠቃሚዎች (በሙሉ ወጣቶች ናቸው) በወርጂ ኮረብታ ወደ የሚገኘው የሥነ ማኅደር ማዕከል የሚመጡ ቱሪስቶችን ተቀብለው ለማስተናገድ የሚያስችላቸውን ሥልጠና ወስደዋል። ይህ አካባቢ ብዙ ዓይነት አእዋፍና እጅግ የሚያምር መልክዓ ምድር ያለው ቦታ ነው። በሥነ ሥርዓቱ መክፈቻ ላይ ከ 200 በላይ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን በዝግጅቱም የባህል ምግቦችንና ተወዳጁን የኢትዮጵያ ቡና አጣጥመዋል። ምግቦቹና ቡናው በየቀኑ በእነዚህ የሥነ ማኅዳር ጥበቃ በሚደረግለት ቦታ በሚገኙት ጎጆዎች ውስጥ ለእንግዶች ይቀርባሉ። የተሰጣቸው የ 100,000 ብር ሥራ ማስጀመሪያ ድጋፍ አባላቱ የራሳቸውን ንግድ እንዲጀምሩና ያንን እንደገና ወደ ደንነት እንዲመለስ የተደረገውን ስፋቱ ወደ 200 ሄክታር የሚጠጋ አካባቢ የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ያግዛቸዋል። ይህንን አካባቢ በአግባቡና በዘላቂነት ለመጠቀም እንዲችሉ የሚያግዟቸው መተዳደሪያ ደንቦች (ሕጋዊ ሰነዶችና መመሪያዎች) በ VoCDA እና IDH ድጋፍ በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች የቁጠባ ቡድን ስብሰባ በሼር ኢትዮጵያ የፕሮጀክት ጅምር ስብሰባ በቀበሌ ደረጃ በሼር ኢትዮጵያ የኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት ምረቃ ስነ-ስርዓት በሼር ኢትዮጵያ የኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት ተሳታፊዎች በሼር ኢትዮጵያ የኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት ስልጠና በሼር ኢትዮጵያ የማህበረሰብ ተሳትፎ ውይይት በሼር ኢትዮጵያ የህብረተሰብ ግንኙነት ስብሰባ በሼር ኢትዮጵያ የንብ እርባታ ስልጠና በሼር ኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክት ተጠቃሚ በሼር ኢትዮጵያ የማህበረሰብ ልማት ውይይት