እ.ኤ.አ. መስከረም 5 በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች አከባቢያቸውን ከቆሻሻ ለማፅዳት ኃይላቸውን አጠናክረው የሚቀሳቀሱበት የጽዳት ቀን ነው። በሼር ኢትዮጵያም በተለምዶ በየሦስት ወሩ ይህ የጽዳት ዘመቻ የሚከናወን ሲሆን በአዲሚ ቱሉ እና በቆቃ እርሻዎቻችንን ላይም እንዲሁ አከባቢን ለማፅዳት በንቃት እንሳተፍለን።
በባቱ /ዝዋይ በሚገኘው እርሻችን ደግሞ ከጎረቤት እርሻዎች ጋር በመቀናጀት እና ሃይልን በማስተባበር በጥቅሉ ከ 100 በላይ የሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞች በየ ሶስት ወሩ በእነዚህ የጽዳት ዘመቻዎች ላይ ይሳተፋሉ።
ጥቃቅን ቆሻሻን ማየት ደስ የማያሰኝ ብቻ ሳይሆን አካባቢውን ይበክልና ወደ ወንዞች ፣ ሐይቆች እና ውቅያኖሶች ይጎዛል በመጨረሻም ስነ ምህዳሩንም ፣ፕላኔቷንም አደጋ ላይ ይጥልና ጤናችንን የሚጎዳ ይሆናል።
በዓመት አንድ ጊዜ ማፅዳት ብቻ ሳይሆን በየሩብ ዓመቱ ሁሉ በትጋት የሚሰሩ ሰራተኞቻችንን እና በጎ ፈቃደኞቻችን ማመስገን እንወዳለን በዚህም መሰረት በመስከረም 5 የዓለም የጽዳት ቀንን ስለምናከብር ሁሉም ሰው ኃይሉን ሰብስቦ እንዲቀላቀለን ጥሪያችንን እናቀርባለን።