ሼር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ሼር ኢትዮጵያ የፅጌረዳ አበባ አምራች ነው። የፅጌረዳ አበባዎቹ ከብረት መዋቅርና የፕላስቲክ ሽፋን በተሠሩ ግሪንሀውሶች ውስጥ ይበቅላሉ። ወደ 12,500 የሚጠጉ ሠራተኞች በሦስት እርሻዎች የፅጌረዳ አበባዎችን ይተክላሉ፣ ይሰበስባሉ፣ ደረጃ ይመድባሉ እንዲሁም ያሽጋሉ። በየዕለቱ ከ2.5 እስከ 4 ሚሊዮን የፅጌረዳ አበባዎች ተቀነባብረው/ተዘጋጅተው አዲስ አበባ ወደ የሚገኘው አየር መንገድ የሚጓጓዙ ሲሆን ከዚህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፓ ውስጥ ወደሚገኙ ተጨማሪ መዳረሻዎች ይላካሉ። ይህም የዓለማችን ትልቁ የፅጌረዳ አበባ አብቃይና የአውሮፓ ትልቁ የፅጌረዳ አበባዎች አቅራቢ ያደርገናል።
ኢትዮጵያ የፅጌረዳ አበባዎችን ለማብቀል እጅግ በጣም ምቹ ሁኔታዎች አሏት፤ ለአብነትም፦ ለም አፈር፣ ተስማሚ የአየር ንብረት፣ በቂ የዝናብ ውሃና ተስማሚ ከፍታ አላት። የአትክልት/ አበባ ዘርፉ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በጣም ወሳኝ ነው። ለዚህ ደግሞ ሼር ኢትዮጵያ ዋነኛው ተዋናይ ሲሆን ወደ 4% የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ፍሰት ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል።
አንዳንዳንድ ትኩረት የሚስቡ ዝርዝሮች፦
- ከ 1 ቢሊዮን በላይ cከካርቦን ልቀት ነጻ በሆነ መንገድ የተመረቱ የፅጌሬዳ አበባዎች በዓመት
- 4,800 ኪሜ በፅጌሬዳ አበባ መደቦች ላይ ውሃ የሚያንጠባጥቡ የውሃ መሥመሮች
- 3,921,500 ሜትር ኪዩብ የዝናብ ውሃ በየዓመቱ ይታቆራል
- በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታልበየዓመቱ ከ100,000 በላይ ለሚሆኑ ታካሚዎች ሕክምና ይሰጣል
- በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 50% የኛ ሠራተኞች ልጆች የሆኑ;ከ 6,500 በላይ ሕፃናት ትምህርት ይማራሉ
- 240,000 ትኩስ ምግብ በየዓመቱ ለኛ ታዳጊ ተማሪዎቻችን በነጻ ይቀርብላቸዋል
- 6,462 ካሬ ሜትር ሰው ሠራሽ ረግረግ ቆሻሻ ውሃን ለማጣራት ጥቅም ላይ ይውላል
- ሼር ኢትዮጵያ በዓለም ትልቁ የፅጌሬዳ አበባ አምራች ነው ርትዓዊ ንግድ
- 116 የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች በኛ የሰው ኃይል ውስጥ እንዲካተቱ ሆነዋል
- ኢትዮጵያ ውስጥ ከ36 በላይ የተለያዩ ወረዳዎች ሠራተኞች ቀጥረን እናሠራለን።