ዘላቂነት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች

የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) “ለሁሉም ፍጡር የተሻለና የበለጠ ዘላቂ ወደፊትን ለማሳካት እንደ ረቂቅ መነሻ ሆነው እንዲያገለግሉ” ታስበው የተዘጋጁ የ17 እርስ በርሳቸው የሚገናኙ ዓለም አቀፍ ግቦች ስብስብ ናቸው። እንደ ሼር ኢትዮጵያ ለእነዚህ ግቦች ጠቃሚ አስተዋጽኦዎችን እናደርጋለን።

በድህነት ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች የሚካሄድ የ16 አፓርታማዎች ግንባታ

የሼር ኢትዮጵያ የርትዓዊ ንግድ ፕሪሚየም ኮሚቴ/ Sher Fairtrade Premium Committee በቅርቡ ዝዋይ ውስጥ ለ16 በድህነት ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦች አፓርታማ/ የጋራ መኖሪያ ሕንጻ/ እንዲገነባ ወስኗል። ይህ ለእነዚህ የማኅበረሰቡ አባላት ቀደም ሲል ያጡትን ሰላማዊ የመኖሪያ ቤትና ንጹሕ የመጸዳጃ አገልግሎት መስጫዎችን በማቅረብ ጠየናማ የመኖሪያ ቦታ እንዲያገኙ ለማረጋገጥ ያስችላል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

በየዓመቱ 240.000 ትኩስ ምግቦችን ማቅረብ|የሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል

ሁሉም በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የአጸደ ሕፃናት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ 1,200 ተማሪዎች በየዕለቱ ጠዋት ላይ ትኩስ ምግብ በነጻ ይቀርብላቸዋል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

የሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል

ሆስፒታላችን በየዓመቱ ከ100,000 ለሚበልጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጣል። የሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞችና ተማሪዎች ነጻ የጤና እንክብካቤ የሚያገኙ ሲሆን የአካባቢው ማኅበረሰብ ንዑስ የሆስፒታል ክፍያዎችን ብቻ በመክፈል አገልግሎቱን ያገኛል። የሆስፒታሉ 75 የጤና ባለሙያዎችና 90 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በየዕለቱ ለክልሉ ደኅንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች

ሼር ኢትዮጵያ በሦስት ቦታዎች ከ6,500 ለሚበልጡ ሕፃናት ትምህርት ያቀርባል። የአጸደ ሕፃናት፣ የአንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱ ለሠራተኞች ልጆችና ለሌሎች የማኅበረሰቡ አባላት በነጻ ይቀርባል። ቆቃ ውስጥ ሼር ኢትዮጵያ ለአካባቢ የመንግሥት ትምህርት ቤት መገንባትና አስተዳደር ርዳታ ያደርጋል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

የጾታ እኩልነትን ማሳካትና የሁሉንም ሴቶችና ልጃገረዶች አቅም ማጎልበት

በሥርዓተ ጾታ፣ የሴቶችን አቅም ማጎልበትና አካታችነት ላይ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እናቀርባለን፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሴቶችና ወጣት ልጃገረዶች ርዳታ እናደርጋለን።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

በገጠር አካባቢዎች ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በዝዋይ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር ነዋሪ ለሆኑ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ቤተሰቦች ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እያቀረብን ነው። በቦቼሳና ዋጂራ ዋሽጉላ የመጠጥ ውሃ ቱቦዎችን በተለያዩ አቅጣጫዎች በማራዘም በተለያዩ ቦታዎች የውሃ ቦኖዎችን ገንብተናል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

ከ12.500 ለሚልቁ ሠራተኞች የሥራ ዕድል መስጠት

ከ15 ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ሼር ኢትዮጵያ በአገሪቱ የአበባ ልማት ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድራጊ ሲሆን ወደ 4% የሚጠጋ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት ወደ አገር ውስጥ እንዲመጣ ለማድረግ አስችሏል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

አደጋ የሚቋቋም መሠረተ ልማት መገንባትና አካታችና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ማስፈንና ፈጠራን ማሳደግ

3 የአበባ እርሻ ማሳዎች በየዓመቱ ከ1 ሚሊዮን አስተማማኝ ዘላቂ የፅጌሬዳ አበባዎችን ያመርታሉ።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

ዕድሜን፣ ጾታን፣ አካል ጉዳትን፣ ዘርን፣ ብሔርን፣ የዘር ሀረግን፣ ሃይማኖትን ወይም የኢኮኖሚ ወይም ሌላ ደረጃን ፍጹም መሠረት ሳናደርግ የሥራ ዕድሎችን እናቀርባለን

በሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞችን ከ36 የተለያዩ ወረዳዎች የምንቀጥር ሲሆን ለሠራተኞቻችንና የማኅበረሰቡ አባላት ብዝኃነት አቀፍና አካታች ሠራተኛ ኃይል የመፍጠር ቁርጠኝነታች መገለጫ የሆኑ የተለያዩ ፕሮግራሞችና የሥልጠና ኮርሶችን በማቅረባችን ኩራት ይሰማናል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

ሼር ኢትዮጵያ የሥራ ዕድሎች፣ ትምህርት፣ ጤናና በጠቅላላው ልማት በማቅረብ አስተዋጽኦ ያደርጋል

የሥራ ቦታዎቻችንን ደኅንነትና ንጽሕና ከመጠበቅ በተጨማሪ የዛፍ ችግሮችን እናቀርባለን እንዲሁም እንተክላለን። የአካባቢ አርሷደሮችን እናስተምራለን። ለንጹሕ ውሃ ተደራሽ እናደርጋለን።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

በአካባቢ ወይም በማሳዎቻችን የሥራ ሁኔታዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሳናደርስ ለደንበኞቻችን በከፍተኛ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ የፅጌሬዳ አበባዎችን እናቀርባለን

ዘላቂ አመራረት፦ IPM፣ Wetlandsና የጠብታ መስኖ አማካኝነት። በFairtrade አማካኝነት ዘላቂ ፍጆታ እንዲኖር ማድረግ

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

በቅርቡ እንደ ኩባንያ የካርቦን ልቀትን እጅግ ዝቅተኛ የማድረግ ደረጃ ላይ በመድረሳችን ኩራት ይሰማናል

ይህ ማለት ፅጌረዳ አበባዎቻችንን በምናመርትበትም ሆነ በምንሸጥበት ወቅት የምንተወው የካርቦን ልቀት አሻራ በጣም ዝቅተኛ ነው።.

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

በጠብታ ተጨማሪ ሰብል

ሼር ኢትዮጵያ ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ልዩ ዝግ የሉፕ ሲስተም የሚጠቀም ሲሆን ሲስተሙ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው ውሃን ለማጥለልና መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ነው። wetlands ተብለው የሚጠሩት ሁሉንም ቆሻሻ ውሃ ያጣራሉ። ውሃው ከተጣራ በኋላ የፅጌሬዳ አበባዎችን በመስኖ ለማልማት ጥቅም ላይ ይውላል።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

የተራቆተ መሬትን ወደነበረበት መመለስ

የደን ሽፋንን ወደነበረበት እንዲመለስ ለመርዳትና የዝናብ ውሃ ማጠንፈፍን ለማስተዋወቅ ባለፉት ዓመታት ውስጥ በዝዋይ ሐይቅ የላይኛው ተፋሰስ 800,000 ችግኞችን ተክለናል። በአሁኑ ወቅት ወደዚህ ቦታ የዱር እንስሳት እየተመለሱ ነው።

ስለዚህ አስተዋጽኦ በተመለከተ ተጨማሪ ያንብቡ

አጋርነቶች

ዘላቂ ልማት ለማምጣት በምናደርጋቸው ጥረቶች የተለያዩ አጋሮችን ማለትም Floriculture Sustainable Initiative፣ IDH፣ የአካባቢ፣ የክልልና የፌደራል መንግሥት አካላት፣ የኢትዮጵያ የቤተሰብ መምሪያ ማኅበርና የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሚይዙ ኃይሎች ጥምረትን ተቀላቅለናል።