ሼር ኢትዮጵያ ለሠራተኞቹ ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን መፍጠሩን እያረጋገጠ ከዚህ ጎን ለጎን ዘላቂነት ባለው መልኩ ፅጌሬዳ አበባዎችን የሚያመርት በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል። የአመራረት ሂደታችንና ሥርዓታችን በተለያዩ ደረጃ መዳቢና መርማሪ አካላት ምርመራ ተደርጎባቸው ስለ ብቃታቸው ምሥጋና የተጎናፀፉ ናቸው።
- Fairtrade
- MPS-SQ
- MPS-ABC
- MPS-GAP
- GRASP
- ETI
- EHPEA የሥራ ሥነ ምግባር የብር ሜዳሊያ ደረጃ ዕውቅና
- EHPEA የሥራ ሥነ ምግባር የወርቅ ሜዳሊያ ደረጃ ዕውቅና
እነዚህን የምስክር ወረቀቶች ለማየት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን አገናኝ (ሊንክ) በመጠቀም ለማየት ይችላሉ፦
ርትዓዊ የንግድ ውድድር
ለሠራተኞቻችን ውጤታማ የመኖሪያና የሥራ ሁኔታዎችን መፍጠርንና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የአመራረት ሂደት ረገድ የተለያዩ የርትዓዊ የንግድ ውድድር መስፈርቶችን እናሟላለን። በርትዓዊ የንግድ ውድድር ስም ሥር የሚሸጡ የፅጌሬዳ አበባዎች ሸማቾች በመጠኑ ከፍ ያለ ዋጋ የሚከፍሉ በመሆኑ ተጨማሪ ገቢ ያስገኛሉ። ይህ ተጨማሪ ገቢ በከፊል በሼር ኢትዮጵያ ለሚካሄዱ እንደ ሆስፒታሎችና ትምህርት ቤቶች ለመሳሰሉ የማኅበራዊ ፕሮጀክቶች ጥቅም ላይ ይውላል። በተጨማሪም ለገለልተኛ የ Fairtrade Premium Committee ለሚመደበው በጀት ሌላ አስተዋጽኦ ሲኖረው፣ ይህም በጀት የምግብ ቅመማ ቅመሞችን ግዢ ለመደጎምና ለሠራተኞች ሥልጠና ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላል። ስለሆነም በአውሮፓ የሚገኙ ሸማቾች በኢትዮጵያ የተሻሉ የአኗኗር ሁኔታዎች ለመፍጠር በተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ሼር ኢትዮጵያ የርትዓዊ የንግድ ውድድርን ደረጃዎች የሚያሟላ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ በየዓመቱ ቁጥጥር ይካሄድበታል።
የMPS ማኅበራዊ ብቁነት ማረጋገጫ
ጥሩ የሥራ ድባብን መፍጠር ለብዙ ነጋዴዎችና ሸማቾች ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የMPS ማኅበራዊ ብቁነት ማረጋገጫ (MPS -Socially Qualified (SQ)) የምስክር ወረቀት በጤናና ደኅንነት ዘርፍ የዓለም አቀፍ መስፈርቶች (የሥነ ምግባር ደንብ) መሟላታቸውን ያረጋግጣል።
MPS-ABC
MPS-ABC ኩባንያዎች ተገቢ እርምጃዎችን በመውሰድ በአካባቢ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጉዳቶችን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል የሚያሳይ የመቆጣጠሪያ ዘዴ ነው። MPS-ABC ግልጽና በቁጥር ሊለኩ የሚችሉ ከዘላቂነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥረቶችን በቁጥር አንድ ሁለት ተብለው እንዲቆጠሩ ያስችላል። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለው ምስክር ወረቀት የሚሰጠው ምርትን መጠበቂያ ዘዴዎች፣ የኃይል አጠቃቀም፣ የማዳበሪ አጠቃቀም፣ ውሃና ፍሳሽ አጠቃቀም በዲጂታል መንገድ መመዝገቡን በማረጋገጥ የሚሰጥ የአካባቢ ጥበቃ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ነው። ይህ እኛ የተሸለምነው የMPS-A የብቃት ማረጋገጫ አካባቢን ካገናዘበ አመራረት ተነጥሎ የሚታይ አይደለም።
MPS-GAP (መልካም የግብርና ሥራ ሥነ ምግባር)
MPS-GAP ክትትል ማድረግ መቻልን፣ አካባቢ ጥበቃን፣ ደኅንነትና ንጽሕና አጠባበቅን አስመልክቶ የሚከናወን የብቃት ማረጋገጫ መስጫ መርሐ ግብር ነው። MPS-GAP የ GlobalGAP ተምሳሌት ተደርጎ የተወሰደ ሲሆን የምስክር ወረቀቱ እንደተሰጠ ወዲያውኑ GGN (የ GlobalGAP ቁጥር) ይመደባል። ቁጥሩ በ GlobalGAP ማዕከላዊ የመረጃ ቋት ላይ በግልጽ ይታያል።
GRASP
GRASP (የGlobal GAP የማኅበራዊ አሠራር የሥጋት ጥናት) አንድ ድርጅት ባለው የ MPS GAP የምስክር ወረቀት ላይ በተጨማሪነት የሚሰጥ ምስክር ወረቀት ነው። የGRASP ሞጁል የኩባንያዎችን የሠራተኞችና የደሞዝ ክፍያ ሁኔታ፣ ጡረታና ሥራን ለሦስተኛ ወገን በተቋራጭነት መስጠት በመሳሰሉ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ስለመሟላታቸው ምዘና ያደርጋል።
ሥነ ምግባር የተከተለ የንግድ እንቅስቃሴ (ETI - Ethical Trading Initiative)
ETI በዋናነት የተዘጋጀው ለእንግሊዝ (ዩኬ) ገበያ ነበር። በሌላ በኩል የ MPS ማኅበራዊ ብቁነት ማረጋገጫ (MPS-Socially Qualified) ለሁሉም አገራት በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን የመያዶችና የንግድ ማኅበራት ሰፊ ዓለም አቀፍ ድጋፍ አለው። ሥነ ምግባር የተከተለ የንግድ እንቅስቃሴ (ETI) ከMPS ማኅበራዊ ብቁነት(MPS-Socially Qualified) ጋ ብዙ ተመሳሳይነቶችያሉት ቢሆንም በዋንኛነት ግን ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው በአበባ ጅምላ ነጋዴዎችና አቅራቢ ኩባንያዎች ላይ ነው።
EHPEA የሥራ ሥነ ምግባር የብር ሜዳሊያ ደረጃ ዕውቅና
ይህ በኢትዮጵያ የሆርቲካልቸር አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር የሚሰጥ መለያ ምልክት በኢትዮጵያ የማኅበሩ አባል የሆኑ የአበባ፣ የተክሎችና አታክልት ላኪዎችን የማኅበራዊና የአካባቢ ጥበቃ አፈጻጸምን ደረጃ ይቆጣጠራል። የEHPEA የሥራ ሥነ ምግባር ደንብ ሦስት እርከኖች ያሉት ሲሆን እነዚህም፦ ነሐስ፣ ብርና ወርቅ ናቸው። የብር ሜዳሊያ ደረጃ የሥራ የሥነ ምግባር ለአበባዎችና ማስዋቢያዎች ደረጃው በ Global GAP ከሚሰጠው ምስክር ወረቀት ጋ ተመጣጣኝ ነው። የቁጥጥር ማኅበር ማረጋገጫ ሰጪ ተቋም (Control Union Certification (CUC) በማረጋገጫ አሰጣጡ ሂደት ገለልተኛ ቁጥጥር በማድረግ ምስክር ወረቀት ይሰጣል።
EHPEA የሥራ ሥነ ምግባር የወርቅ ሜዳሊያ ደረጃ ዕውቅና
ከብር ሜዳሊያ ደረጃ የሥራ ሥነ ምግባር ዕውቅና (Code of Practice Silver) ጋር ሲነጻጸር የወርቅ ሜዳሊያ ደረጃ ከአካባቢው ማኅበረሰብና ከአበባ ምርት ዘርፉ ጋ ተጨማሪ ሥራዎችን መሥራትንና ትብብር መፍጠርን ይጠይቃል። ሼር ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 (2008 ዓ.ም.) የወርቅ ሜዳሊያ ደረጃ ዕውቅናን አግኝቷል።
አን ሲሚንታ
የደንብ ተገዢነት ማረጋገጥ ሥራ ኃላፊ