ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው 8ኛው የሆርቲፍሎራ ኤግዚቢሽን ላይ ሶስት አስደሳች ቀናትን በታላቅ ደስታ መለስ ብለን ሰንመለከት፣ ኤግዚቢሽኑ የተከፈተዉ በግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ሲሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ለእኛ ኤግዚቢሽኑ ከብዙ ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር ስለ እርሻዎቻችን እና ውብ ጽጌረዳዎቻችንን በዘላቂነት ስለምናመርትበት መንገድ ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረ ነበር። ብሎም ስለ ብዙው የCSR ፕሮጄክቶቻችንና፣ የእንቦጭ አረምን ከሀይቁ ላይ ለማሰወገድ በሚደረገው ዘመቻ የአካባቢውን ሴቶች በማስልጠን የተለያዪ ዓይነት የእጅ ስራ ምርቶችን አረሙን በመጠቀም አምርተዉ ለገበያ እንዲያቀርቡ በማድረግ የምናበረከተውን አስተዋጽኦ ጨምሮ ለመግልጽ ችለናለ፡፡
በዚህ አመት የኤግዚቢሽኑ መሪ ቃሉ ዘላቂነትን ማረጋገጥ’ የሚል ነበር እና ከEHPEA (Gold certificate Code of Conduct) and MPS (Hortifoot print Calculator) የተባሉ ሽልማቶችንም በማግኘታቸን እንኮራለን።
በአጠቃላይ የተሳካ ኤግዚቢሽን ነበር እና ሁሉንም ጎብኝዎቻችንን በዚሁ እጋጣሚ ለማመሰገን እንውዳለን።