ማኅበራዊ ኃላፊነት

የሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል

Sher hospital from above

የሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የተቋቋመው በ2007 ዓ.ም. ሲሆን እንደ አገር አቀፍ ሆስፒታል ሆኖ ያገለግላል። የዝዋይና አካባቢው ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት ወደ 600,000 የሚጠጋ ሲሆን ሆስፒታሉ በየዓመቱ ከ100,000 ለሚበልጡ ታካሚዎች አገልግሎት ይሰጣል። በቀን ወደ 300 ያክል ታካሚዎች ሕክምና ያገኛሉ። የሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞችና ተማሪዎች ነጻ የሕክምና እንክብካቤ የሚያገኙ ሲሆን የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት አነስተኛ የሆስፒታል ሕክምና ክፍያዎች ይከፍላሉ። 75 የጤና ባለሙያዎችና 90 ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በየዕለቱ ለክልሉ ደኅንነት/ ጤናማነት ከፍተኛ ጥረቶችን ያደርጋሉ።

አንዳንድ የሆስፒታሉ ባሕሪያት፦
  • 24/7 ክፍት የመጀመሪያ ሕክምና ርዳታ፤
  • 140 የሆስፒታል አልጋዎች፤
  • 2 የማምከኛ ቀዶ ሕክምና ክፍሎች፤
  • በ2020 (እ.አ.አ) በDutch Flower Foundation በርዳታ የተሰጠ አዲስ የኤክስሬይ/ ራጅ ማሽን፤
  • መመርመሪያ ላብራቶሪ፤
  • መድኃኒት ቤት፤
  • የጥርስ ሐኪም፤
  • የፊዚዮቴራፒ ሕክምና ክፍል።

የሆስፒታል ሠራተኞች ስለ የቤተሰብ ምጣኔና የወሊድ ቁጥጥር በተመለከተ የምክር አገልግሎት ያቀርባሉ። በተጨማሪም የክትባት ፕሮግራሞችን ለማቅረብ ከመንግሥት ድርጅቶች ጋር አብረን እንሠራለን። የVCT መምሪያ በቅድመ መከላከል፣ እንክብካቤና የኤችአይቪ ኤድስ ታማሚዎች ድጋፍ ላይ ርዳታ ያደርጋል።

ኮቪድ-19

protect_yourself_and_othersሆስፒታላችን ስለ COVID-19 ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የአካባቢውን ማኅበረሰቦች ንጽሕናን ስለመጠበቅና ማኅበራዊ ርቀትን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት ለማስተማር የተለያዩ ዘመቻዎች ተካሂደዋል። እ.ኤ.አ በኅዳር 2021 ዓ.ም.ና በየካቲት 2022 ዓ.ም. ሠራተኞቻችንንና ተማሪዎቻችንን ለመከተብ ትላልቅ ዘመቻዎች ተካሂደው ነበር። ከ12.000 የሚበልጡ ሰዎች ለመከተብ ፍላጎት ነበራቸው።

ስለ ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የተመለከቱ አስተያየቶች