ዘላቂነት

መልሶ በደን መሸፈንና ሥነ ምህዳሮችን ወደነበሩበት መመለስ

restore_landscapes

IDH እና Self Help Africa ጋር በጋራ በመሥራት የተራቆቱ መሬቶችን እንዲያገግሙ ለማድረግ እየሠራን እንገኛለን። በኢትዮጵያ ዛፎች በዋናነት ለግንዲላነትና የማገዶ እንጨትነት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከመሆኑ አንጻር አገሪቱ እየተራቆተች ነው ማለት ነው። ስለሆነም ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የደን ሽፋንን ወደነበረበት ለመመለስና የዝናብ ውሃ ማቆርን ለማስተዋወቅ በዝዋይ ሐይቅ የላይኛው ተፋሰስ 800,000 ችግኞች ተተክለዋል። በዋጅራ ኮረብታ ላይ ወደ 200 ሄክታር በሚጠጋ ቦታ ላይ የዛፍ ችግኞች ተተክለዋል። ቦታው የተመረጠው በአካባቢው ማኅበረሰብ ነው። በዛፎች መካከል የሚበቅሉት ሣሮች ለእንስሳት መኖነት ያገለግላሉ። የተመረጡት የዛፍ ችግኞች ፍራፍሬ የሚያበቅሉ መሆናቸው ደግሞ ፍራፍሬዎቹ በሚደርሱበት ወቅት ለማኅበረሰቡ በምግብነት እንዲያገለግሉ ለማድረግ ያስችላል። ይህ ማለት ዛፎቹ ለሁለት ዓላማ ያገለግላሉ ማለት ነው። ይህን በደን መልሶ የመሸፈን ሥራ ለማገዝ ለ250 አርሷደሮች በአፈርና ውሃ መከላከያ መዋቅሮች ግንባታ፣ የእንስሳት መኖ ዝግጅትና በሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች አስተዳደር/አያያዝ ክኅሎቶች ላይ ሥልጠና ተሰጥቷል።

የዱር እንስሳት ሀብት አሻራዎች