የእርሻዎቻችንንና የደረጃ ምደባ ሥራዎቻችንን በአግባቡ ለመሥራት ተገቢ የቴክኒክ ድጋፍ መኖሩ ወሳኝነት አለው። ስለሆነም የሙያ ዘርፉ ለሼር ኢትዮጵያ ወሳኝ ዘርፍ ነው! ጀነሬተሮች ያለ ምንም ችግር መሥራት ይኖርባቸዋል፤ ግሪንሀውሶች ተገቢ ጥገና ያስፈልጋቸዋል እንዲሁም ማሽኖችና መሣሪያዎች ደኅንነታቸው ተጠብቆና ለመጠቀም ዝግጁ ተደርገው መያዝ አለባቸው። ይህ በሥራችን ውስጥ አስፈላጊ መምሪያ ከመሆኑም ባለፈ የቴክኒክ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ይፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪም ሁሉንም የግንባታ ሥራዎች የምናከናውነው በራሳችን አስተዳደር ነው።
ስንታየሁ ማንፈርዶ / ከፍተኛ የብየዳ ሥራ ባለሞያ
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
ለሼር ኢትዮጵያ መሥራት የጀመርኩት ከ2011 (2003 ዓ.ም.) ጀምሮ ነው።
እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
ለሼር ኢትዮጵያ መሥራት የጀመርኩት በእርሻ ላይ ጠቅላላ ሠራተኛ ሆኜ ነበር። ቀጥዬም ወደ ስካውት ቡድን ተቀላቀልኩ። እራሴን የማሻሻል ጉጉት የነበረኝ በመሆኑ የማታ ትምህርት ተከታትዬ በደረጃ አራት የብየዳ ሥራ ባለሙያነት ተመረቅኩኝ። አሁን የኩባንያው ከፍተኛ የብየዳ ሥራ ባለሙያ ሆኜ እየሠራሁ እገኛለሁ።
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
ተወልጄ ያደግኩት ዝዋይ ውስጥ ነው። በትውልድ ከተማዬ ውስጥ እንደዚህ ዓይነጥ በጣም ጥሩ ሥራ ማግኘት ትልቅ ዕድል ነው። ለቤተሰቤ መቅረብ የምፈልግ እንደመሆኑ እዚህቨ ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ በመሥራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።
ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
አዎ፦ ሼር ኢትዮጵያ ከደመወዝ በተጨማሪ እንደ ትምህርት ቤት የመሳሰሉ ሌሎች የጥቅማ ጥቅም መርሀግብሮች ያሉት በመሆኑ ምክንያት ብዙ ወጣቶችን ወደዚህ መጥተው እንዲሠሩ እመክራለሁ፤ ለምሳሌ ያክል የሠራተኞች ልጆች በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የመማር ዕድል የሚያገኙ ሲሆን ሕፃናቱ ከ0-12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን የሚከታተሉት ያለ ምንም ክፍያ ከመሆኑም በተጨማሪ ምንም የሕክምና ወጪዎች አይከፍሉም። ሌላኛው ትልቁ መርሐ ግብር የሆስፒታል ሕክምና ሲሆን የትኛውም ሠራተኛ በሚታመምበት ወቅት ሁሉም የሕክምና ወጪዎቹ በኩባንያው የሚሸፈኑ ሆኖ ይህም የሪፈራል ጉዳዮችንም ይጨምራል።
ቦኖ ራጎ / መካኒክ
በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመሩት መቼ ነበር?
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት የጀመርኩት ከመጋቢት 2013 (2005 ዓ.ም.) ጀምሮ ነው።
እባክዎ ስላለፉበት የሙያ ዕድገት ይንገሩን
በሼር ኢትዮጵያ መጀመሪያ ላይ የተቀጠርኩት በጥበቃ ሠራተኝነት ነበር። ከሥራ ሰዓት ውጭ ትምህርቴን እየተከታልኩ የመካኒክነት ሙያ አጠናሁ። ከተመረቅኩ በኋላ ኩባንያው ወደ ሜካኒካል መምሪያ አሳደገኝ። አሁን ከኩባንያው ሜያተኛ መካኒኮች መካከል አንዱ መሆን ችያለሁ።
ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራትን የሚወዱት ለምንድን ነው?
በመጀመሪያ ሥራ መሥራትና ቤተሰቤን መደገፍ እፈልጋለሁ። በሁለተኛ ደረጃ ኩባንያው በትውልድ ቦታዬ የሚገኝ በመሆኑ ሥራ ለማግኘት ሌላ ትግል ማድረግ አያስፈልገኝም። በሦስተኛ ደረጃ በሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሰው በተለይም እራሱን የማሻሻልና የመማር ፍላጎት ካለው ይበረታታል። ከሁሉም በላይ ግን ኩባንያው ክፍት የሥራ መደብ ሲኖር ለሠራተኞቹ ቅድሚያ ይሰጣል።
ሌሎች ሰዎችን ሼር ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቀጠር እንዲያመለክቱ የሚመክሩት ለምንድን ነው?
አዎ፦ እኔ አሁን እያገኙ ያለኋቸውን እንደ የትምህርትና የሆስፒታል መርሀግብሮች የመሳሰሉ ጥቅማ ጥቅሞችን ሌሎች ሰዎችም እንዲያገኙ ስለምፈልግ ለሼር ኢትዮጵያ እንዲሠሩ እመክራቸዋለሁ። ለሼር ኢትዮጵያ መሥራት ሕይወታቸውን እንደሚቀይረውም ለማስረዳት እፈልጋለሁ።