ስለ እኛ ማንነት

በሼር ኢትዮጵያ ተቀጥሮ መሥራት

በሆርቲካልቸር ጥበብ በየቀኑ ልዩነትን እንፈጥራለን

ለሼር ኢትዮጵያ ተቀጥሮ መሥራት በዓለም ግዙፉ የፅጌሬዳ አበባ አምራችና በኢንዱስትሪው ግንባር ቀደም ለሆነው ድርጅት መሥራት ማለት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ለረዥም ዘመናት የተካበተ አበባ የማምረት ልምድና ተሞክሮ አለን። ወደ 12,500 ገደማ ሠራተኞችን እስካሁን ድረስ ቀጥረን በማሠራት ላይ ነን። ለሼር ኢትዮጵያ ተቀጥረው ሲሠሩ በግል ሕይወትዎ ከሚያገኙት ዕድገት ባሻገር ሌሎች በመስኩ ከፍተኛ የሞያ ዕውቀት ካላቸው ሠራተኞች ጋ አንድ ላይ እንደ ቤተሰብ ሆነው መሥራት የሚችሉበትን ዕድል ያገኛሉ።

ዋና ዋና ዕሴቶቻችንና የድርጅታችን መርሆዎች፦ ለሥራችን ጥልቅ ፍቅር ያለን መሆን፣ አጋሮቻችንን ማክበር፣ የቡድን አባላት ብዝኃነትና ሁሉን አቃፊነት፣ ዘላቂነት ያላቸው ስትራቴጂዎች መኖር።

ከኛ ሠራተኞች ጋ ይተዋወቁ
ዕሴቶቻችንና የጋራ እምነታችን

ለሥራ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው
ሠራተኞች

ቀና የሆነ አስተሳሰብን እናራምዳለን፤ የሌሎችን ሐሳብ እናከብራለን እንዲሁም ሁልጊዜም የተናገርነውን በተግባር እንፈጽማለን። የነፍስ ወከፍና የወል አቅማችንን ከዕለት ወደ ዕለት እናሻሽላለን።

አጋሮችን
ማክበር

ከደንበኞቻችን፣ ከሌሎ ች አበባ አምራቾችና የአካባቢ ማኅበረሰቦች ጋ ሐቀኝነትን፣ አመኔታንና ግልጽነት የተሞላ በመተማመን ላይ የተመረኮዘ የትብብር መንፈስን እንፈጥራለን። ለእኛ እንዲደረግልን በምንፈልገው ዓይነት አቀባበልና መስተንግዶ ሌሎችን ሰዎች ተቀብለን እናስተናግዳለንን፤ በጋራም እናድጋለን።

የቡድኖች
ብዝኃነት

lከተለያዩ ቡድኖች የተለያዩ አስተሳሰቦች ይመነጫሉ፤ እኛ ሁሉንም አካታች ነን፣ ከስሕተቶቻችን እንማራለን እንዲሁም ስኬታችንን በጋራ እናከብራለን። ደካማ ጎናችንን ሳንደብቅ በተጠያቂነትና በታማኝነት እንሠራለን።

ዘላቂ
ስትራቴጂዎች

ከግቦቻችንን ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ጉጉት አለን፤ ውሳኔ ስንሰጥ በመረጃ ላይ ተመርኩዘን ይሆናል፤ የምርት አቅርቦታችን በቴክኖሎጂ ተደግፎ ይከናወናል። የድርጅታችንን አባላት፣ የአካባቢያችንን ማኅበረሰብና ያለንበትን አካባቢ መፃዒ ሕይወት የተሻለ ለማድረግ የአጭርና የረዥም ጊዜ ስትራቴጂ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ አሰጣጥ ዘዴን እንጠቀማለን።