Overview News

አፍሪፍሎራ፣ ደች ፍላወር ግሩፕ እና ካማራ ኤዱኬሽን በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ሁለት የIT ክፍሎችን በጋራ አዘምነዋል።

3 July 2023 Aswin Endeman

በደች ፍላወር ፋውንዴሽን እና በአፍሪፍሎራ ለጋስነት በዝዋይ በሚገኘው ሼር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ሁለት አዲስ የኢ-መማሪያ ማዕከላትን ማቋቋም ችለናል።

ካማራ ኤዱኬሽን 50 አዳዲስ ኮምፒውተሮችን እና ሁለት ሰርቨሮችን የተከለ ሲሆን ፣ ኮምፒውተሮችን ለት/ቤት የሚያቀርብ እንዲሁም መምህራንን እያሠለጠነ፣  በገጠር እና ሩቅ በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች  ለትምህርት ምቹ የሆኑ የኮምፒዩተር ክፍሎችን በማቋቋምና አስተማማኝ እንዲሁም ከወረቀት እና ከአቧራ-ነጻ አካባቢን በመፍጠር ያግዛል።

አሰልጣኞችም ለአንድ ሳምንት ያህል በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ተገኝተው 26 መምህራንን የኮምፒዩተር አጠቃቀም በስርአተ ትምህርቱ መሰረት በማሰልጠን እና በመሰረታዊ ጥገና ላይ ምክር ሰጥተዋል።

የካማራ  ኮምፒውተሮች በኡቡንቱ ክፍት ምንጭ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ይሰራሉ። ከቀላል  እስከ ልዩ የካማራ መማሪያ ስቱዲዮ ግብአቶችን ለሂሳብ እና ለሳይንስ የተለያዩ ትምህርታዊ ሶፍትዌሮች ተጭነዋል። ብሎም ኮምፒውተሮቹ እንዲሁ ከመስመር ውጭ የሆነው ዊኪፔዲያም ተጭኖላቸዋል፣ ይህም ውስን የበይነመረብ ግንኙነት ላላቸው ትምህርት ቤቶች ያልተለመደ የመማሪያ ምንጭ ይፈጥራል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ኮምፒውተሮቹ በፒዲኤፍ የተጫኑ የትምህርት ሚኒስቴር የመማሪያ መጽሃፍቶች አጠቃላይ የትምህርት ቤቱን ሥርዓተ ትምህርት ያካተቱ ናቸው። በብዙዎቹ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች 40,000 ለሚጠጉ የመማሪያ መጽሀፍት አቅርቦት በጣም ውስን በመሆኑ ይህ ብቻውን ጥሩ ግብአት ይሆናል።

የደች ፍላወር ፋውንዴሽን  የተቸገሩ ሰዎችን እና በተለይም የህጻናትን የኑሮ ሁኔታ እና ደህንነት ለማሻሻል ያለመ ነው።   የደች ፍላወር ቡድን (DFG) አጋሮቹ በተገኙበት ቦታ የማህበረሰብ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር የሚሰራ ነው። ቡድኑም /DFG ለምንኖርበት አለም ያለውን ሀላፊነት እየተወጣ ይገኛል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችም በዚህ ተጠቃሚ ይሆናሉ ይላሉ የሼር ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ አጋ፡ የኮምፒውተር ችሎታ ለተማሪዎቻችን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ሼር-ትምህርት ቤት  በኢትዮጵያ ጥሩ ስም ካላቸው ት/ቤቶች ውስጥ አንዱ ነው። ሁሉም ተማሪዎች ማለት ይቻላል ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ብቁ ይሆናሉ። አዳዲሶቹ የኮምፒውተር ክፍሎቸም ስማችንን ብሎም ደረጃችንን እንድናስጠብቅ እና ዲጂታል አለምን ለተማሪዎቻችን እንድንከፍት ያስችሉናል።

አፍሪፍሎራ በኢትዮጵያ ውስጥ ሼር ኢትዮጵያ በሚል ስም ሶስት እርሻዎች አለው። በሼር ትምህርት ቤቶች 6800 ልጆች ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ትምህርት  በነፃ  ያገኛሉ።

ደች ፍላወር ግሩፕ እና ካማራ  በዚህ ፕሮጀክት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላቅ ያለ አድናቆት  ያለን ሲሆን በተማሪዎቹ እና በመምህራን ስም ከልብ ለመምስገን እንወዳለን።