Overview News

ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ

17 March 2023 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ የኤክስፖ ማዕከል

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው 8ኛው የሆርቲፍሎራ ኤግዚቢሽን ላይ ሶስት አስደሳች  ቀናትን በታላቅ ደስታ መለስ ብለን ሰንመለከት፣ ኤግዚቢሽኑ የተከፈተዉ በግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ሲሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ለእኛ ኤግዚቢሽኑ ከብዙ  ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር ስለ እርሻዎቻችን እና ውብ ጽጌረዳዎቻችንን በዘላቂነት ስለምናመርትበት መንገድ ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረ ነበር። ብሎም ስለ ብዙው የCSR ፕሮጄክቶቻችንና፣ የእንቦጭ አረምን ከሀይቁ ላይ ለማሰወገድ በሚደረገው ዘመቻ የአካባቢውን ሴቶች በማስልጠን የተለያዪ ዓይነት የእጅ ስራ ምርቶችን አረሙን በመጠቀም አምርተዉ ለገበያ እንዲያቀርቡ በማድረግ  የምናበረከተውን አስተዋጽኦ  ጨምሮ ለመግልጽ ችለናለ፡፡

በዚህ አመት የኤግዚቢሽኑ መሪ ቃሉ ዘላቂነትን ማረጋገጥ’ የሚል ነበር እና ከEHPEA  (Gold certificate Code of Conduct) and MPS (Hortifoot print Calculator) የተባሉ  ሽልማቶችንም በማግኘታቸን  እንኮራለን።

በአጠቃላይ የተሳካ  ኤግዚቢሽን ነበር  እና ሁሉንም ጎብኝዎቻችንን በዚሁ እጋጣሚ ለማመሰገን እንውዳለን።

የሼር ኢትዮጵያ የኤክስፖ ቦታ የሼር ኢትዮጵያ የኤክስፖ ማዕከል በሆርቲፍሎራ ኤክስፖ የሼር ኢትዮጵያ ዝግጅት የሼር ኢትዮጵያ EHPEA የምስክር ወረቀት በሆርቲፍሎራ ኤክስፖ ላይ የሼር ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ዝግጅት Ekisipoo Hortifilora keessatti agarsiisa abboota qabeenyaa Sheer Ethiopia