Overview News

ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል አዲስ የማደንዘዣ መስጫማሽን ግዢ አከናወነ፡፡

25 October 2022 Aswin Endeman

በባቱ/ዝዋይ ከተማ የሚገኘው ሼር ኢትዮጵያ  ሆስፒታል አገልግሎቱን ለማሻሻል ባደረግነው ጥረት በቅርቡ አዲስ የማደንዘዣ መስጫማሽን ግዢ አከናዉኗል። የማደንዘዣ ሰጪ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ወርቄ አቦይ በሰጡት አስተያየት በማሽኑ አንድ ጊዜ ማደንዘዣዉን ለበሽተኛዉ ከተሰጠ በኃላ ሙሉ በሙሉ በራሱ  የሚሰራ በመሆኑ የማደንዘዣ ሰጪ ባለሙያዉ በሽተኛውን እየተከታተለ በቀዶ ጥገናው ስራ ላይ ተጨማሪ እርዳታን መስጠት ያስችለዋል ብለዋል።

ሌላው የአዲሱ ማሽን ጥቅም ደግሞ የሕፃናትን የቀዶ ጥገና ሕክምና  መስጠት የሚያስችል  መሆኑን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደምሳቸዉ ጌታቸዉ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል፡- ‘ከዚህ ቀደም ህጻናት ቀዶ ጥገና ሲያሰፈልጋቸዉ ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች  የምንልክ የነበረ ሲሆን አሁን ግን አዲሱን ማሽን በመጠቀም ህክምናዉን በዚሁ በራሳችን ሆስፒታል መስጠት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡

ማሽኑም በክፍሉ ከተተከለ እና  ለሚመለከታቸው ሁሉም የክፍሉ ሰራተኞች በአምራች ድርጅቱ ባለሙየዎች  ሙያዊ ስልጠና, ከተሰጠ በኃላ ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ ይውሏል ፡፡

በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል ሁሉም የሼር ሰራተኞች  ማለትም በቁጥር 12.500 የሚሆኑ  እና የሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት -ተማሪዎች  እንዲሁ ወደ 6.500 የሚደርሱ በሙሉ ነፃ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ። የአካባቢዉ ማህበረሰብ  ደግሞ በዝቅተኛ ዋጋ የሚገለገሉ  ሲሆን ይህም ሆስፒታሉ  በየዓመቱ ከ100,000 በላይ ታካሚዎችን   እንደሚያክም ተገልጻል፡፡