ባለፈው ሳምንት በፌርትሬድ መርሃግብር ስር ባለው DONUTS program ፕሮግራም በኩል የተለያዩ የአካል ድጋፍ መስጫ መሳሪያዎችን ማግኘት የቻልን ሲሆን ከነዚህም ውስጥ መነጽር ፣ ክራንቾች፣ ምቹ ጫማዎች ፣ሰው ሰራሽ እግሮች ቁጥራቸው ከፍ ላለ ሰራተኞቻችን ማሰራጨት ችለናል።
ይህም ለ 4 ዓመታት የሚዘልቅ መርሃ ግብር ሲሆን ዓላማዎቹም የሥርዓተ ጾታ እኩልነት ፣ ወጣቶች እና ተጋላጭ የሆኑ ቡድኖችን እና በተለይም የአካል ጉዳተኞችን ማበርታት እና መደገፍ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ መርሃግብሩ የፌርትሬድ ምርት አምራች ድርጅቶችን አቅም እና የሠራተኛ ማህበራትንም አቅም ለማጎልበት ዓላማ ያለው ፕሮግራም ሲሆን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የገንዘብ ድጋፍም ተደርጎለታል።
ሼር ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ማካተት ሁል ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፣ ስለዚህም የ DONUTS ፕሮግራም ለ108 የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞቻችን በመሳሪያ በመደገፉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።
በዚህ ፕሮጀክት ሼር ኢትዮጵያ እና ፌርትሬድ አፍሪካ ከ ግራር ቤት ተሃድሶ ማህበር ጋር ተባብረዋል ማህበሩም የተጠየቀውን የመሣሪያ አይነት እና መሳሪያዎቹም በትክክለኛ ሁኔታ መገጣጠም እንዲችሉ ለመወሰን ይረዳ ዘንድ ለተጠቃሚዎች ልኬቶችን በቅድሚያ አከናውኗል በዚህም መሰረት ቀደም ተብሎ የተጠቀሱት ክራንቾች ፣ ሰው ሰራሽ እግሮች ፣ ምቹ ጫማዎች መነጽር እና መስማት የሚያስቸሉ መሣሪያዎችን ለ108 ሠራተኞቻችን ማዳረስ በመቻላችን እናም እነሱም በምቹ ሁኔታ መኖር እና መሥራት መቻላቸውን በማየታችን ደስተኞች ነን። ለተከበሩ አጋሮቻችንም የላቀ ምስጋናችንን በድጋሚ እናቀርባለን።