Category Archives: News

Overview News

ለሼር ሆስፒታል አዲስ አምቡላንስ

29 November 2024 Mariska Braam
የሼር ሆስፒታል ሰራተኞች አምቡላንስ ስልጠና ሲወስዱ

ማክሰኞ ነሀሴ 14 ከፍተኛ የድረጅቱ ሀላፊ ሚስተር ፌርሪክ ብሩንሰማ እና የኦፕሬሽን ሀላፊ ሚስተር አስዊን ኤንደመን ፣ የህብረተሰብ  ተወካይ የተከበሩ እንግዳ አባ ገዳ አብዱራማን ደቀቢ ፣ የባቱ/ዝዋይ ጤና ጣቢያ ተወካይ  አቶ ፈይሳ ሌንጂሶ በተገኙበት አዲስ ብራንድ ሚኒባስ አምቡላንስ ለሼር ሆስፒታል በመሰጠቱ እኛ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶናል.

በተካሄደው ስነስራት አባገዳ የሆኑት አብዱራማን የምስጋና ንግግር እና አፍሪ/ሼር ለሆስፒታሉ ተጨማሪ አምቡላንስ በማበርከቱ አመስግነው አምቡላንሱ ለሆስፒታሉና ለህብረተሰቡ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ገልፀዋል.

በአፍሪ ፍሎራ/ሼር በኩል ሚስተር አስዊን ኤንደመን ይህን አምቡላንስ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ድርሻ ያላቸውን በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምቡላንሱን ለማጓጓዝ ባደረገው አስተዋፆ አመስግነዋል በመጨረሻም የሆስፒታሉ ባለሙያዎች አስፈላጊነት ፣ በቀጣይ ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤ ለሰራተኞች እና ለህብረተሰቡ በቁርጠኝነት ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን እውቅና በመሰጠት የአምቡላሱን ቀልፍ ለሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ደምስ እና ለሆስፒታል ማናጀር ኑራ ነጋዮ ተረክቦዎል፡፡

በተደረገው ስነስርዓት አምቡላንሱ ለስራተኛ እና ህብረተሰቡ ለሪፈራልና ድንገተኛ ጥሪ እንደተጨማሪ አቅም እና ለህክማና ቡድንለመደበኛ ስራቸው ድጋፍ እንዲሆነ በመግለፅ አምቡላንሱ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሼር ሆስፒታል ሰራተኞች አዲሱን አምቡላንስ ሲመለከቱ የሼር ሆስፒታል አዲስ አምቡላንስ ውስጣዊ ክፍል የሼር ሆስፒታል ሰራተኞች አምቡላንስ ስልጠና ሲወስዱ የሼር ሆስፒታል አዲስ አምቡላንስ ፊት ለፊት እይታየሼር ሆስፒታል አዲስ ነጭ አምቡላንስ ርክክብ ስነ-ስርዓት

Overview News

ደች ፍላዎር ፋውንዴሽን ለሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል BS-200E ኬሚስትሪ ማሽን ለገሰ

5 July 2024 Mariska Braam
የሼር ሆስፒታል ባለሙያዎች አዲሱን ማሽን ሲመለከቱ

በባቱ /ዝዋይ የሚገኘውን የሼር ሆስፒታል አገልግሎቱን ለማሻሻል ባደረግነው ጥረት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆነ BS-200E ኬሚስትሪ ማሽን ለመግዛት ከደች ፍላዎር ፋውንዴሽን ከፍተኛ ልገሳ አግኝተናል። ይህ መሣሪያ ብዙ አይነት ሪኤጀንቶችን መጠቀም የሚያስችል ያልተገደበ አሰራልን የያዘ ነው ስለሆነም ሆስፒታሉ በጥሩ ዋጋና ጥራት የተለያዩ የሪኤጀንት ዓይነቶችን ከገበያ በመግዛት አገልግሎቱን እንዲሰጥ ያስችለዋል ።

የላቦራቶሪ ክፍል ሃላፊ  የሆኑት አቶ ሱራፌል ከበደ እንደተናገሩት ምርመራን በአፋጣኝ ለማከናወን ብቃት ያላቸው ሠራተኞች ብቻ ሳይሆኑ ዘመናዊ የሆኑ የላቦራቶሪ ማሽኖች  ሲሟሉ ስርአቱ ወይም ደንቡ የሚጠይቀውን ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠትን እንደሚያስችል ይገልፃሉ። ላቦራቶሪ ክፍሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ክፍሎችን በማስፋፋትን፣ ነባር መሣሪያዎችን በአዲስ በመተካት እና ሠራተኞችንም  የማሠልጠን ፕሮግራሞችን ጨምሮ ታላላቅ ማሻሻያዎችን አድርጓል። አዲሱ የኬሚስትሪ መመርመሪያ ማሽንም አገልግሎታችንን ይበልጥ ለማሻሻል ይረዳናል ሲሉ ፣ አክለውም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የሼር ሆስፒታል ሠራተኞች  የሁል ጊዜ ተባባሪያቸው የሆነውን  የደች ፍላወር ፋውንዴሽንን አመስግነዋል።

በሼር ሆስፒታል ውስጥ ሁሉም የሼር ሰራተኞች ( 12.500 የሚጠጉ) እና የሼር-ተማሪዎች (6.500 የሚሆኑ) ነፃ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ። እንዲሁም የህብረተሰቡ አባላት በአነስተኛ ወጪ ይገለገላሉ። በየዓመቱ ከ100.000 የሚበልጡ ታካሚዎች በሆስፒታሉ ሕክምና ይደረግላቸዋሉ።

የደች አበባ ፋውንዴሽን (DFF) አላማውም የተቸገሩ ሰዎችን በተለይም ህፃናትን የኑሮ ሁኔታ እና ደህንነት ለማሻሻል ጥረት ያደርጋል።

የሼር ሆስፒታል BS-200E ማሽን ዝርዝር እይታ የሼር ሆስፒታል ባለሙያዎች አዲሱን ማሽን ሲመለከቱ የሼር ሆስፒታል አዲስ BS-200E ኬሚስትሪ ማሽን

Overview News

የአካል ጉዳት ላለባቸው የሼር ሰራተኞች የአካል ድጋፍ መስጫ መሳሪያዎች ተበረከተላችው

3 July 2024 Mariska Braam
የሼር ሆስፒታል የአካል ድጋፍ መሳሪያዎች ስጦታ

በሼር ኢትዮጵያ የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰራተኞችን ማካተት የተለመድ ተግባር ነው። ስለዚህም በፌይርትሬድ አፍሪካ ዶናት ፕሮግራም ውስጥ በቁጥር 70 የሚሆኑ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች ይበልጥ ምቹ በሆነ መንገድ ስራቸውን  እንዲሠሩ ሊረዳ የሚያስችሏቸው የአካል ድጋፍ መስጫ መሣሪያዎች ተበርክቶላቸዋል ለዚህም ምስጋናችን ከልብ ነው።

የመጀመሪያውን ዙር ጨምሮ በጠቅላላው 178 ሰራተኞች ከዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ  ማድረግ ተችሏል።

በዚህ ፕሮጀክት ሼር ኢትዮጵያ እና ፌርትሬድ አፍሪካ በዝዋይ ከሚገኘው ከግራርቤት የተሃድሶ ማህበር ጋር በመተባበር ተጠቃሚዎቹ ምን ምን አይነት መሳሪያ እንደሚያስፈልና የሚያስፈልጉትንም የመሳሪያዎቹ ትክክለኛነትና ተስማሚነት ለመወሰን ልኬት እንዲፈፅሙ ይደረጋል። ከእነዚህም መካከል  ባለ ሦስት ብስክሌቶች፣ ምርኩዝ፣ ሰው ሠራሽ እጅና መነጽር እንዲሁም መስማትን የሚያግዙ መሣሪያዎች ይገኙበታል።

ፌይርትሬድ አፍሪካ እና ግራርቤት የተሃድሶ ማህበር ላከናወኑት ታላቅ ስራ እና ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን

የሼር ሆስፒታል ሰራተኞች የአካል ድጋፍ መሳሪያ ርክክብ የሼር ሰራተኛ አዲስ የእግር መርጃ መሳሪያ ሲጠቀም የሼር ሆስፒታል የአካል ድጋፍ መሳሪያዎች ስጦታ የሼር ሰራተኛ የአካል ድጋፍ መሳሪያ ሲረከብ

Overview News

ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል አዲስ ዲጂታል የጥርስ ኤክስሬይ ማሽን አስገባ

23 May 2024 Mariska Braam
የሼር ሆስፒታል አዲስ ዲጂታል የጥርስ ኤክስሬይ

በቅርቡ ትልቅ እድሳት የተደረገለት የጥርስ ክሊኒኩ፣ አሁን ላይ ሁለት የጥርስ ህክምናን መስጫ ወንበሮች  ያሉት ሲሆን ይህም የህክምና ሂደቱን የበለጠ ውጤታማ  ሊያደርገው ችሏል ። በተጨማሪም ዘመናዊ ያልነበርዉ የኤክስሬይ ማሽን በተንቀሳቃሽ ዲጂታል ኤክስሬይ  ማሽን በመተካቱም ፊልም ከመጠቀም ይልቅ ፎቶ ለማንሳት ኤሌክትሮኒክ የሆነ ዘዴን እንድንጠቀም አስችሎናል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የኤክስሬይ ቴክኖሎጂን ስንጠቀም ኬሚካሎች ያስፈልጉ ነበር. ከዚህም በላይ ብዙ ጊዜም ይ ወስዷል ስለሆነም የምስሎቹ ጥራት ከዲጂታል ኤክስሬይ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛም ነበር። ለዚህም ነው ተንቀሳቃሽ ዲጂታል ኤክስሬይ  ማሽን መግዛት ያስፈለገው።

የክፍሉ የጥርስ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ነጻነት አበበ ፡ ”በክሊኒካችን ውስጥ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል ኤክስሬይ  ማሽን   በመጨመሩ  በጣም ደስተኛ ነኝ ፣ ዲጂታል ኤክስሬይ ማሽኑ  የታካሚዎቻችንን ፍሰት የበለጠ ቀልጣፋ በማድረግ ና ተፈላጊዉን የታካሚዎቻችንን የጥርስ ክፍል ለማየት ያስችለናል ሲሉም አክለዋል”።

ሼር ኢትዮጵያ ለሰራተኛው፣ ለሼር-ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ለማህበረሰብ አባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ባለው ሆስፒታሉ ላይ ኢንቨስት ማድረጉን ይቀጥላል።.

በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የተገጠመው አዲስ ዲጂታል የጥርስ ኤክስሬይ ማሽን የሼር ሆስፒታል ዲጂታል የጥርስ ኤክስሬይ ስራ ላይ የሼር ሆስፒታል አዲስ ዲጂታል የጥርስ ኤክስሬይ

Overview News

የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል የፍጥነት መገደቢያዎች ከዝዋይ እስከ አዳሜ ቱሉ ባለው መንገድ ላይ ተቀመጡ

3 May 2024 Mariska Braam
በዝዋይ-አዳሜ ቱሉ መንገድ ላይ የሚገኙ የፍጥነት ገዳቢዎች

በኢትዮጵያ,  እርሻዎቻችን  በሙሉ ከአዲስ አበባ ሞያሌ በሚያገናኘው ዋና መንገድ ተጓዳኝ ላይ ይገኛሉ። ይሁንና አዲስ የተሰራውም የፍጥነት መንገድ የመንገደ ትራፊክ መጨናነቅን ቢቀንስም፣ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም ብዙ የትራፊክ አደጋዎች በመንገዶቹ ላይ ይስተዋላሉ  ስለዚህም  ፍጥነትን የሚቀንሱ የመንገድ ላይ ጉብታዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ላለፉት ጊዜያቶች ስንታትር የነበረው በዚህም የተነሳ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በቦታው በመገኘት በእርሻዎቻችን አካባቢ በአጠቃላይ 6 የፍጥነት  መገደቢያ ጉብታዎችን አስቀምጦ የነበረው ለትብብሩም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከልብ ለማመስገን እንወዳለን። በመጨረሻም ለሰራተኞቻችን እና ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት   እንደሚያስገኙ ተስፋ እናደርጋለን።

በዝዋይ-አዳሜ ቱሉ መንገድ ላይ የተተከሉ የደህንነት መሳሪያዎች በዝዋይ-አዳሜ ቱሉ መንገድ ላይ የተሰሩ የፍጥነት መቆጣጠሪያዎች በዝዋይ-አዳሜ ቱሉ መንገድ ላይ የሚገኙ የፍጥነት ገዳቢዎች በዝዋይ-አዳሜ ቱሉ መንገድ ላይ የተተከሉ የፍጥነት መቆጣጠሪያዎች

Overview News

አካታች በሆነ መልኩ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8/2024 በሼር ኢትዮጵያ ተከበረ

26 March 2024 Mariska Braam
በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች ቀን ዝግጅት ላይ የተሰበሰቡ ሰራተኞች

መጋቢት 8 እና 9 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (IWD) በሼር ኢትዮጵያ ተከበረ. Inspire Inclusion የዚህ ዓመት የአለም አቀፍ ጭብጥ  መርህ ነበር፣ እናም በዚህ መሰረት የተለያዩ የውይይት መድረኮች  ተዘጋጅተውም ነበር።

በዕለቱም መጋቢት 8 በድርጅቱ COO አስዊን ኢንዴማን እና በኦፕሬሽን ዳይሬክተሩ አንድሪው ብሩክ ስሚዝ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ፕሮግራሙ የተከፈተ ሲሆን በንግግራቸውም ላይ ሁሉንም ሰራተኞች ላይ በእኩል፣  በንቃት ሲሰራበት እና የሁሉንም ባልደረቦችንን አስተዋፅኦ ስንመለከት ለኩባንያው መሳካት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል።።

ከዚያ በኋላ የሥርዓተ-ፆታ ኮሚቴው በኔዘርላንድ ውስጥ በምትገኝ ዞተርዎዴ ከተማ ምክር ቤት ሴቶች ጋር በበይነ መረብ ስብሰባ በማድረግ በአንድ ላይ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እያከበሩ ነበር፣ በዛም ተያይዞ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እና እርስ በእርስ ለመማማር አበረታች መንገድም አግኝተው ነበር።

መጋቢት 9 ከሁሉም ሰራተኞቻችን ጋር በመሆን በድጋሚ IWD በእርሻችን ላይ አክብረንም ነበር። ይህም በዝዋይ እርሻ ላይ በመግቢያው በር ላይ የፎቶ መነሻ ቦርድ   የተዘጋጀ ሲሆን የስርዓተ-ፆታ ኮሚቴውም ሰራተኞችን በሙዚቃ እና በዳንስ ሲቀበል ነበር በዚህም መርሃ ግብር ውስጥ ብዙ ፎቶግራፎች የተወሰዱ ሲሆን ለብዙዎችም ቀኑ ጥሩ እና አስደሳች የሆነ የስራ ቀንም ነበር።

ወደ ሼር ኢትዮጵያ ለስራ የሚመጣ ሰራተኛ ሁሉ ስለግል ንፅህና ምቾት እንዲሰማው እና አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት መስጠት ይፈልጋል፣ በዚህ ምክንያት ኩባንያው ‘Mela for her’ መላ ለእርሷ የሚባል እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እሽጎችን በሁሉም እርሻዎች ላይ ለአበባ ቆራጮች አከፋፍሏል። እንዲሁም በቀጣይ ለሌላ ክፍል ሴት ሰራተኞችም እንዲሁ የሚደርስ ይሆናል።

በመጨረሻም በዝዋይ እርሻ በሚገኘው መዝናኛ አዳራሽ ውስጥ የሥርዓተ-ፆታ ኮሚቴው ከሴቶች መብት፣ ከሥርዓተ-ፆታ እኩልነት፣ ከሴቶች በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶችና ስኬቶች የሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

በኩባንያው ውስጥ የሴቶችን ስኬት ያከበርንበት እና አካታች ስራንም ለመስራት ያነሳሳንበትን ታላቅ ቀን መለስ ብለን ስንመለከትም መሪ ቃሉን ‘Invest in women እድገትን ለማፋጠን ይረዳል’ መማለት ሁላችንም ይህንን እንድናስታውስ እና ቀን ከቀን የስራችን አንዱ አካል ልናደርገውም ይገባናል።

በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች ቀን ዝግጅት ላይ የተሳተፉ ሴቶች በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች ቀን ዝግጅት ላይ የተሰበሰቡ ሰራተኞች በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች ቀን ስብሰባ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች ቀን አከባበር ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች በሼር ኢትዮጵያ የሴቶች ቀን በዝግጅት ላይ የሚገኙ ሴት ሰራተኞች

Overview News

350 ሴት ልጆች እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መላ ለእርሷ የተሰኘ የንፅህና መጠበቂያ ፓድዎች ተለግሰዋል

12 January 2024 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ የተለገሱ የንፅህና መጠበቂያ ፓድዎች

በ2015 መኸር ላይ የተጀመረውን ፕሮጀክት ተከትሎ፣ በቅርቡ በሼር ትምህርት ቤቶቻችን እድሜያቸው ከ12 እስከ 13 ዓመት የሆናቸው 350 ሴት ልጆች እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የንፅህና መጠበቂያ ፓድዎችን ሰጥተናል. ይህ ሊሆን የቻለው በኔዘርላንድ የአበባ ፋውንዴሽን ከፍተኛ ድጋፍ ነው።

መላ በአማርኛ መፍትሄ ማለት ሲሆን የሚያመለክተውም በሚያሳዝን ሁኔታ በአፍሪካ ውስጥ ለብዙ ወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ላለው ችግር መፍትሄ ማበጀት ሲሆን ይህም ተመጣጣኝ የሆነ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች እጥረትን ለማቃለል ያሰበ ሲሆን በአፍሪካ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጃገረዶች ለትምህርት፣ ለጤና፣ በራስ  ካለመተማመን በላይ ለሰብአዊ መብቶች እንቅፋት ይፈጥራል ብሎም ለብዙዎች የወር አበባ መጀመር ማለት በትምህርት ቤት ውስጥ ቀሪ እንዲበዛም ያደርጋል።

መላ እርሷ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን በመላው ኢትዮጵያ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የወር አበባ ምርቶችን እና የወር አበባን የጤና ትምህርት በመስጠት ህይወትን የሚቀይር የኢትዮጵያ ማህበራዊ ጀማሪ ድርጅት ነው.

በዚህ ፕሮጀክት፣ ሼር-ትምህርት ቤቶች፣ መላ ለእርሷ እና የደች አበባ ፋውንዴሽን ተባብረዋል. የባለሙያዎች ቡድኑ ፓድ ከመስጠቱ በተጨማሪ የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን በማሰልጠን በልጃገረዶች ክበብ በኩል ሁሉም ልጃገረዶች በወር አበባ ጤና ላይ ስልጠና ይሰጣቸዋል.

መላ እርሷ ለቡድኑ ፍሬያማ ትብብር ማመስገን እንፈልጋለን እንዲሁም የደች አበባ ፋውንዴሽን ላደረጉት የማይናወጥ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን. ልጃገረዶች በህይወት ውስጥ ያላቸውን ሙሉ አቅም እንዲደርሱ በማስቻል የክብር መብታቸውን የሚደሰቱበት ዓለም በጋራ እናበረክታለን።

በሼር ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ፓድ ስጦታ ስነ-ስርዓት በሼር ኢትዮጵያ የተደራጀ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ፓድ ስጦታ ስነ-ስርዓት Sher Ethiopia: Kennaa paadii laguu shamarran dargaggootiif በሼር ኢትዮጵያ የተለገሱ የንፅህና መጠበቂያ ፓድዎች

Overview News

የአረጋውያን ቀን አከባበር

2 January 2024 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የአረጋውያን ቀን አከባበር

በቅርቡ በባቱ/ዝዋይ ተከበረውን የአረጋውያን ቀንን ስፖንሰር በማድረግ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ አረጋውያን ያበረከቱትን አስተዋጾ ለማክበር እና ለመዘከር እንዲሁም ለማድነቅ የተዘጋጀ ድንቅ ቀን ነበር። ዝግጅቱ የአረጋውያን   ጠቃሚ ሚና በመገንዘብ ልምዳቸውን ለተተኪው ትውልድ የሚያካፍሉበት መድረክ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመም ነበር።

ክቡር አቶ አህመዲን እስማኤል (የከተማው ከንቲባ) ካደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በፊትም ከዚህ አለም በሞት የተለዩትን የአረጋውያን በማስታወስ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎትም እንዲደረግ አስተባብረው ነበር።

ሼር ኢትዮጵያም ከ500 ኪሎ ግራም በላይ የበቆሎ ዱቄት እና 50 ሊትር የምግብ ዘይት ለ50 አረጋውያን በስጦታ መልክ  በማስረከብ ለዝግጅቱ ያለውን ተሳተፎም በቀናነት አሳይቷል።

በሼር ኢትዮጵያ የአረጋውያን ቀን ማክበሪያ ዝግጅት በሼር ኢትዮጵያ የአረጋውያን ቀን ክብረ በዓል በሼር ኢትዮጵያ የተዘጋጀ የአረጋውያን ቀን አከባበር

Overview News

በድጋሚ ጌሪት ኤንድ ኔል ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለ 4 ተማሪዎች ተሰጠ

14 December 2023 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ የባርንሆርን ስኮላርሺፕ ስጦታ ስነ-ስርዓት

በቅርቡ ለሶስተኛ ጊዜ የጌሪት ኤንድ ኔል ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለአራት 12ተኛ ክፍልን ላጠናቀቁ የሼር ትምህርት ቤት ተማሪዋች ተሰጥቷል።እንደሚታወቀው የባርንሆርን ቤተሰብ የሼር ኢትዮጵያ እና የትምህርት ቤቶቹ መስራቾች ናቸው.።በየዓመቱ 4 ተማሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በመረጡት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚማሩበት ወቅት አብዛኛውን የጥናት ወጪያቸውን እና ኑሮዋቸውን ለማገዝ ይረዳ ዘንድ በስኮላርሺፕ መልክ በየወሩ ገንዘብ በሼር ኢትዮጵያ በኩል ይላክላቸዋል። የስኮላርሺፑ ዋና አላማ የተቸገሩ ሆነዉ ነገርግን ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ለመርዳት የሰበ ነው።

ስለዚህም፟ ፣ተማሪ ነኢማ አስቻሌው፣ ጀሚላ ሄዴቶ፣ መሀመድ አህመድ እና ዮርዳኖስ ሻንበል ሽልማታቸውን ከወይዘሮ ሉሊት ታዴለ እና ከ ሚስተር አስዊን ኢንዴማን  አጅ ተቀብለዋል። ሼር ማኔጅመንትን በመወከልም ሚስተር አስዊን ኢንዴማን    አሸናፊዎቹን እንኳን ደስ ያላችሁ  በማለት እና የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን እና ደጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ላለፉት 16 አመታት ላደረጉት ትጋት አና ላስመዘገቡት ውጤት አመስግነዋል።

ከሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተመራቂዎች ውስጥ 8 ተማሪዎች ተመርጠው 4ቱ ለስኮላሺፕ ሲሰጣቸው ሌሎች 4 ደግሞ ላፕቶፕ ተሸልመዋል ስሥነ ሥርዓቱም የተካሄደው የተማሪ ቤተሰቦች፣ የሸር ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጆች፣ የማኅበረሰብ ሽማግሌዎች፣ የሼር ትምህርት ቤት ሠራተኞች፣ የወላጅ ኮሚቴ እና በርካታ የመንግሥት የከተማዉ አመራሮች በተገኙበት ነው።

አንደሁልጊዜው ሁሉ ጌሪት ባርንሆርን፣ ባለቤታችው ፣ ልጆቻቸው ላለፉት አመታት ለሼር ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታል ላደረጉት የማይናወጥ ድጋፍ አያመሰገንን እነዚህ ተማሪዎች ሼር ኢትዮጵያ ላስመዘገበው አወንታዊ ተፅእኖ እውነተኛ ምሳሌ በመሆናቸው እጅግ ኩራት ይሰማናል ለዝዋይ እና ለአካባቢው ማህበረሰብም ተመልሰዉ አንደሚረዱ አና አንደሚጠቅሙ አምነታችን ነው ሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተመራቂ ተማሪዎቻችን በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ ብሩህ የወደፊት ህይወት እና መልካም ጊዜ እንመኝላቸዋለን።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሼር ትምህርት ቤቶች ከ6500 በላይ ተማሪዎችን በሶስት ቦታዎች ያስተምራሉ፣ በግምት ወደ 400 የሚጠጉ ልጆች ከ 4ዓመት እድማቸው ጀምሮ በየዓመቱ ወደ ሼር ትምህርት ቤቶች ይገባሉ. ምዝገባዉም የሚከናወነው በ 50% ከሼር ሰራተኛ ልጆች እንዲሁም 50% ደግሞ ከአካባቢው ማህበረሰብ ልጆች በሚደረግ እኩል ክፈፈል ነው።

በሼር ኢትዮጵያ የባርንሆርን ስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች በሼር ኢትዮጵያ የባርንሆርን ስኮላርሺፕ ፕሮግራም በሼር ኢትዮጵያ የባርንሆርን ስኮላርሺፕ ስነ-ስርዓት በሼር ኢትዮጵያ የባርንሆርን ስኮላርሺፕ አሸናፊዎች በሼር ኢትዮጵያ የባርንሆርን ስኮላርሺፕ ስጦታ ስነ-ስርዓት

Overview News

ሼር ኢትዮጵያ አዲስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዳሚ ቱሉ ከፈተ

11 December 2023 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ሰፊ መማሪያ ክፍል

በህዳር ወር በቀን 11 ሼር ኢትዮጵያ በአዳሚ ቱሉ አዲስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፈተ። የመክፈቻ ስነስረዕቱም በፕሮገራሙ ላይ ተጋብዘው በነበሩ እንግዶች የተከበሩ አቶ ኡስማን ቱሴ የባቱ ከተማ ምክትል ከንቲባ ፣ አቶ ከዲር ጀቤሶ የባቱ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ፣ ሚስተር አስዊን ኢንድማን የሼር ኢትዮጵያ የቢዝነስ ድጋፍና ሲኤስአር ስራ አስኪያጅ እንዲሁም አዳሚ ቱሉ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ሽማግሌዎች፣ የሼር ኢትዮጵያ አስተዳደር ተወካዮች፣ መምህራን እና በአጠቃላይ ቁጥራቸዉ 192 የሚደርሱ ተማሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።

ትምህርትን ከክፍያ ነፃ መስጠት የሼር ኢትዮጵያ ዋና እሴት ነው. እ.ኤ.አ. በ 2017 ተጀምሮ የነበረው የሁለተኛው እርሻ ግንባታ በአዳሚ ቱሉ በመጠናቀቁ ድርጅቱ በከተማዉ ውስጥ ባሉ አዳዲስ የትምህርት ቤቶች ላይ ኢንቨስት አያደረገ ይገኛል። በ2019 ሼር መዋዕለህፃናቱን በመክፈት የጀመረው ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት 342 ተማሪዎችን ይዞ በማስተማር ላይ ይገኛል። ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላም የመጀመሪያዎቹ የተማሪዎች ማለትም ቁጥራቸው ከላይ የተጠቀሰው በአሁኑ ወቅት በ አዲሱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በመማር ላይ ላይገኛሉ። ሁለቱ ትምህርት ቤቶች በመካከላቸዉ የ500 ሜትር ያህል ርቀት አላቸው።

ሼር በየአመቱ 4 አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት ያቀደ ሲሆን፣ ይህ አዲስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ8 ዓመታት ውስጥ ወደ 1500 የሚጠጉ ተማሪዎች ያይዛል ግቢውም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ለመጨመር በቂ ነው።

የሸር ትምህርት ቤቶች ከሼር ሰራተኞች ለመጡ ልጆች እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመጡ ልጆች አቅም በፈቀደ ሁሉ ክፍት ናቸው።

ይህንን አዲስ ትምህርት ቤት እውን ለማድረግ ለረዱ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው። ከራሳችን የግንባታ ቡድን እስከ ሲቪል ሰርቫንቶች፣ ከመምህራን እስከ ጽዳት ሠራተኞች ድረስ ለሁሉም ምስጋናችን ይድረሳቸው።

ይህ ትምህርት ቤት ለአዳሚ ቱሉ ማህበረሰብ የአንድነት፣ የእድገት እና የዘላቂ መንፈስ ምልክት ይሁን እያልን ብዙዎች የሚማሩበት እና የእውቀት ነበልባል ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው ትውልድ የሚተላለፍበት ቦታ ይሁን ዘንድ ምኞታችን ነው።

የሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ሰፊ መማሪያ ክፍል የሼር ኢትዮጵያ አዲስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህንፃ በአዳሚ ቱሉ Kutaa barnootaa keessaa mana barumsaa Sher Ethiopia በሼር ኢትዮጵያ የአዳሚ ቱሉ ትምህርት ቤት ስጦታ በሼር ኢትዮጵያ የአዳሚ ቱሉ ትምህርት ቤት ክፈታ በሼር ኢትዮጵያ የአዳሚ ቱሉ ትምህርት ቤት ምረቃ በሼር ኢትዮጵያ የተገነባው አዲስ ትምህርት ቤት መክፈቻ